top of page

ከዚያ እስከዚህ ድረስ
ከምስጢረ ድግሴ ፲ኛ ዓመት መታሰቢያ የተጻፈ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አምላከ እስጢፋኖስ
ጠብቀህ አኖርከን ከዚያ እስከዚህ ድረስ
ዛሬ ሁላችሁም እንበል እልል
ቀዳሜ ሰማዕት ቤቱ ተሰርቷል
ብዙ ውጣ ውረድ አልፎ ከፊታችን
ለዛሬ ደርሰናል ተመስገን ጌታችን።

በየደረስንበት ሆነኸን ረዳት
ጎዶላችን ሞልተህ በፀጋ በረከት
መቼ ጣልከን አነተ መቼ ተውከን የትም
ምስጋና ይድረስህ ቸሩ መድኃኒያለም።

ደብረ መዊዕ ቤቴ የስደቴ ቦታ
ከልለሽ ያኖርሽን ከክፍ እይታ
እንኳን አደረሰሽ ለዛሬዋ ቀንሽ
ለአስረኛ ዓመት የልደት በዓልሽ።

ሁሉም ተጠራርቶ ከያለበት ስፍራ
ንሴብሖ ብሎ አምላኩን ሊጣራ
ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስቦልና
በበረከት ጎብኘው ቸር አምላክ ነህና።

ትዝ ይለኛል ያኔ ያለፍት ዓመታት
በአንድ ቄስና በሁለት ዲያቆናት
በሦስት መዘምራን አስር በማይሞሉ በጥቂት አባላት
ነበር ጅማሬችን የዛሬ አስር ዓመት።

መቅደሱን ለማነፅ የጌታውን ቤት
እጅግ ሽቶ ነበር ንጉሱ ዳዊት
አምላክ ሳይፈቅድ ቀረ ባጠፋው ጥፋት
የዳዊትን መሻት ለሰሎሞን ሰጠው
በኢየሩሳሌም ላይ  ህንፃውን አኖው።

እኛም በዚህ ስንኖር በስደት ሃገር
አምላክ እንዲሰጠን ቤተ እግዚአብሔር
ጥቂቶች ብንሆነም የነበረን ቁጥር
በእምነት ተነሳን ከፈጣሪችን ጋር።

በብዙ ውጣ ውረድ በመንከራተት
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ካህናት
ያሉትም ምዕመናን በፍፁም ትጋት
ትንሽ ትልቅ ሳይል አዛውንት ወጣት
በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብ መክረው አብሮ በመስራት
አንድ ዓላማ አንግበው ቤቱን አነጹት።

 

የእስጢፋኖስ ታምር ይገርማል ሳስበው
የትኛውን ትቼ የቱን ልናገረው
እንዲህ ነበር ያኔ ነገሩ የሆነው
ወደሁላ ሄጄ የእሱን ድንቅ ሥራ እንዲህ ሳስታወሰው
ዛሬ በጥቂቱ ምስክርነቱ ትንሽ ልተርከው።

ከሁሉ ከሁሉ የገረመኝ ነገር
የቶማስ መንገድ መፍቀዱ እግዚአብሔር
ገና ስንጀምረው ቤተክርስቲያናችን
በቶማስ ጎዳና ነበር ጅማሬችን
ከዓመታት በኍላ ዳግም ተመልሶ
በቶማስ መንገድ ላይ ታንጾ አየናው ቤተመቅደሳችን።

ነገሩ እንዲህ ነው
አርባ ዘጠነኛው ቶማስ አደባባይ
ቅድሚያ ለስድስት ወር ውልን ተዋውለን
ቃልህን ለመስማት ቤትን ተከራየን
በዚያም በመገልገል ትንሽ እንደቆየን
ውላቸውን አፍርሰው ባልታሰበ ምክንያት ልቀቁ ተባልን።

ሁሉም ተጨናንቆ ለቀጣዩ ሳምንት የት እንሄዳለን ሲል
እሁድ ቀን ሳይመጣ ቀኑ ሳይጎደል
ከነጮች ቤተክርስቲያን ሰፈረ ግላንዴል
 ካህናቱ ሮጠው ትንሿ ቤታችን ተገኘች በአጭርቀን።

የአምላካችን ስራው ለበጎ ነውና
ምንም የሌለውን ሕዝበ ክርስቲያን ፈልጎ ሊያጸና
በባዕድ ሃገር ላይ ግርማ ሞገስ ሆኖን
ያለምንም ክፍያ በነፃ ተገልገሉበት ብለው ፈቀዱልን።

ኩሽናውን አልፈን አጸዳድተን ገብተን
የሚሰቃቀለውን ተባብረን ሰቃቅለን
ጸሎት ቅዳሴችን በጊዜ አከናውነን
መልሰን አጽድተን እናስረክባለን።

ደግሞ እንደዚህ ሆነ
ትንሿ ቤታችን ትንሽ እንደቆየን
ክብረ በዓል ደርሶ መጨናነቅ ያዝን
ማነው የሚያጸዳው ማነው የሚዘምር
ማን ፕሮግራም ይምራ ማነው የሚያስተምር።

ያሉን ካህናቶች ዘማሪዎች ናቸው እንዲሁም ቀዳሾች
እኛው መዘመራን እኛው ምዕመኖች
እንዲያው በአጠቃላይ ምርጫ ስለሌለን
ላለነው አባላት ለአንዱ ሁለት ሥራ
ለሌላኛው ሦስት እንዲሁም በጋራ
ተከፋፈልና በዓልን ለማክበር
እንደ ቻልነው መጠን እንዘጋጅ ጀመር።


 

በዚህ ሁኔታ እንዳለን ቢለንም ድንግርግር
መልካም ዜና ሰማን ከደብረ ሰላሞች ኮሎራዶ ዴንቨር
ወንድሞች እህቶች በአንድ ላይ ተማክረው
በተስፋ ቃል ሞሉን እንመጣለን ብለው።

እንግዳ መቀበል እኛም ወግ ሊደርሰን
በአባታችን ቤት በመላከ መዊዕ በቀሲስ ዮሐንስ
እንግዶቻችን እንጠብቅ ጀመር በሚያጎጎ መንፈስ
ሰላሳ አገልጋዮች በፍቅር ተጠራርተው
አስራ ኣራት ሰዓታት በመኪና ነድተው
መምጣታቸው ሳያንስ ስጦታን አንግበው
ወደ ሰባ የሚሆን የመዘምራን ልብስ ተሸክመው መተው
በፍቅር አስለቀሱን ፍቅር መግበው።

 ምን እነሱ ብቻ ሐመረ ኖሆችም ከባቢሎን ምድር
ከእኛ ጋር ነበሩ አብረው በመዘመር
አንደበተ ርቱዕ መላከ ሳሌም
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በምንም
እኔም ለካሕናት ልብሰ ተክህኖ አንግቼ
አለሁ አባታችሁ አይዞችሁ ልጆቼ
በማለት አጽናነቶ
በየበዓላችን ሁሌ እየተገኘ በትንሿ መቅደስ
አበርትቶን ነበር በጠንካራ መንፈስ።
 
ብዙ ነገር ታልፎ ታነጸና ቤቱ
ሌላ ታምር አየን የቀዳሚ ሰማዕቱን
አይሁዶች ሲወግሩት ቀና ብሎ አይቶ
ማራቸው እንዳለ አይኖቹን ሰክቶ
የዓለማት ፈጣሪ ሥላሴ ተገልጠው
በእራሳችን ቤት ዛሬም በእኛ ዘመን
የሥላሴን ምስጢር ድንቅ ታምር አየን።

ነገሩ እንዲህ ነው
ከሃያ ስድስት ዓመታት በፊት በዚህ የነበሩ
የእግዚአብሔርን ቤት ሊሰሩ ሞከሩ
ከኢትዮጵያ አስመጥተው ታቦተ ሥላሴን
የተቻላቸውን ቢሞክሩም እንካን
እንደ ቅዱስ ዳዊት የልባቸው መሻት
                        በእነርሱ አለተሳካም።

የተቻላቸው ሞክረው ሞክረው
ፈቃደ እግዚሔር እንዳለሆነ ሲያውቁት
ለእህት ቤተክርስቲያን ለግብጻውያኑ በአደራ ሰጡት
ግብፃውያን አባቶች የአጋዕዝተ ዓለምን ታቦት ተረክበው
ንዋየቅድሳት ሁሉንም በአንድ ላይ ይዘው
ለሃያስድስት ዓመታት በገዳማቸው
             ውስጥ በክብር አኑረው
ማንም ሳይወቅሳቸው ጠያቂ ሳይመጣ
በሥላሴ ታምር በእስጢፋኖስ መቅደስ

 

የሥላሴ ታቦት ሰተት ብሎ መጣ።

ይኼ ነው መኖሪያው ይኼኛው ነው ቤቱ
እንኩ ተረከቡን ምዕመን ካህናቱ
ለረዥም ዓመታት አብረነው ኖረናል
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ወደዚህ መርቶናል።

በክብር አኑሩት ከእስጢፋኖስ ጋራ
ሕዝቡ ሁሉ ይደነቅ በአምላካችን ስራ
በማለት አምጥተው ታምሩን ሲያሳዩን
 ግሩም ግብርከ ብለን እኛም አመሰገንን።

እናንት አረጋውያን እናቶች አባቶች
እናነተም ወጣቶች እህቶች ወንድሞች
እንዲሁም ህጻናት በቤቱ ያደጋችሁ
ለዚህ ድንቅ ታምር የተመረጣችሁ
ቤቱን ያነጻችሁ የሥላሴ ልጆች
በአገልግሎታችሁ ናችሁ ተመራጮች
በማያልፈው ዓለም ያርጋችሁ ወራሾች።

ደሞ እስቲ ልመለስ አባቶቼን ላክብር
በትንሿ አንደበት ባልችልም መናገር
እንዲያው ልሞክረው በፈቃደ እግዚአብሔር።

የፀሎት አርበኛ የዋሁ መነኩሴ ገ/ሚካኤል ቆሞስ
በሌሊት ተገኝቶ ለዓለማት ፈጣሪ ምስጋናን የሚያደርስ
 ያለውን አካፋይ የመጣ የሄደውን ብሉ እና ጠጡ ባይ
ምግበ ሥጋንና ምግበ ነፍስን ጭምር
ሕዝብን በንስሐ በሥጋ ወደሙ ያበቃ ለክብር
አምላኩን ጠዋት ማታ በክብር ለምኖት
 ይኸው ለዛሬ ቀን በክብር አቆመው ለአስረኛ ዓመት
ረዥሙን እድሜ አምላክ ይስጥልን
ዘወትር በፀሎቱ እንዳይለየን።
 

ለዚህ ሁሉ ምክንያት መርጦት እግዚአብሔር
ከድቁና አንስቶ እስከ ክሕነት ክብር
በቤቱ ያፀናው አንገቱን የደፋው በስነምግባር
አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሁሉን በፍቅር
በወጣትነቱ ፍፁም ትህትህትና ሰጥቶት እግዚአብሔር
መሰባሰብ ፈጥሮ በማስተባበር
የደብሩ አስተዳዳሪ ይገባዋል ክብር
አገልጋይ ካህን ነው ብቻ ነው እንዳንለው
ምስጢሩን ፈልፈሎ ሲያስተምር አየነው
ስብከተ ወንጌሉን ቁጭ ብሎ ለሰማው
በእርጋታ ሆኖ ለተከታተለው
እውነተኛው መምህር መላከ መዊዕ ነው
እናቶች አባቶች ወጣቶች ሕጻናት ተገኝተው በመቅደስ
ተንትኖ ሲያስረዳ መጽሐፈ ወንጌልን ልክ እንደ ጳውሎስ

በዚህ ሁኔታ እንዳለን ቢለንም ድንግርግር
መልካም ዜና ሰማን ከደብረ ሰላሞች ኮሎራዶ ዴንቨር
ወንድሞች እህቶች በአንድ ላይ ተማክረው
በተስፋ ቃል ሞሉን እንመጣለን ብለው።

እንግዳ መቀበል እኛም ወግ ሊደርሰን
በአባታችን ቤት በመላከ መዊዕ በቀሲስ ዮሐንስ
እንግዶቻችን እንጠብቅ ጀመር በሚያጎጎ መንፈስ
ሰላሳ አገልጋዮች በፍቅር ተጠራርተው
አስራ ኣራት ሰዓታት በመኪና ነድተው
መምጣታቸው ሳያንስ ስጦታን አንግበው
ወደ ሰባ የሚሆን የመዘምራን ልብስ ተሸክመው መተው
በፍቅር አስለቀሱን ፍቅር መግበው።

 ምን እነሱ ብቻ ሐመረ ኖሆችም ከባቢሎን ምድር
ከእኛ ጋር ነበሩ አብረው በመዘመር
አንደበተ ርቱዕ መላከ ሳሌም
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በምንም
እኔም ለካሕናት ልብሰ ተክህኖ አንግቼ
አለሁ አባታችሁ አይዞችሁ ልጆቼ
በማለት አጽናነቶ
በየበዓላችን ሁሌ እየተገኘ በትንሿ መቅደስ
አበርትቶን ነበር በጠንካራ መንፈስ።
 
ብዙ ነገር ታልፎ ታነጸና ቤቱ
ሌላ ታምር አየን የቀዳሚ ሰማዕቱን
አይሁዶች ሲወግሩት ቀና ብሎ አይቶ
ማራቸው እንዳለ አይኖቹን ሰክቶ
የዓለማት ፈጣሪ ሥላሴ ተገልጠው
በእራሳችን ቤት ዛሬም በእኛ ዘመን
የሥላሴን ምስጢር ድንቅ ታምር አየን።

ነገሩ እንዲህ ነው
ከሃያ ስድስት ዓመታት በፊት በዚህ የነበሩ
የእግዚአብሔርን ቤት ሊሰሩ ሞከሩ
ከኢትዮጵያ አስመጥተው ታቦተ ሥላሴን
የተቻላቸውን ቢሞክሩም እንካን
እንደ ቅዱስ ዳዊት የልባቸው መሻት
                        በእነርሱ አለተሳካም።

የተቻላቸው ሞክረው ሞክረው
ፈቃደ እግዚሔር እንዳለሆነ ሲያውቁት
ለእህት ቤተክርስቲያን ለግብጻውያኑ በአደራ ሰጡት
ግብፃውያን አባቶች የአጋዕዝተ ዓለምን ታቦት ተረክበው
ንዋየቅድሳት ሁሉንም በአንድ ላይ ይዘው
ለሃያስድስት ዓመታት በገዳማቸው
             ውስጥ በክብር አኑረው
ማንም ሳይወቅሳቸው ጠያቂ ሳይመጣ
በሥላሴ ታምር በእስጢፋኖስ መቅደስ

 

ትምህርቱን ስንማር በቀሲስ ዮሐንስ
ቃለ እግዚአብሔርን የሥላሴን ምስጢር
የመጽሃፉን ትርጉም ሁሉን ሲያመሰጥር
ይህ ወጣቱ ካህን ይህ ወጣት መምህር
ነገሮቹን ሁሉ የሚያመዛዝን
ለእኛ ለሁላችን ምሳሌ እንዲሆን
አምላከ እስጢፋኖስ መምህር ሰጠን
የልጆችህ አባት የዕድሜ ባለጸጋ አምላክ ያድርግልን
በተዋሕዶ አጽንቶ ከዚህ የበለጠ ለማየት ያብቃን።

በእውነት ታድለናል እግዚአብሔር ባርኮናል በዚቹ ቤታችን
ትላንት ትንሽ ሆነን እንዳልተጨናነቅን
ከተለያየ ስፍራ በምሑር ዲያቆናት ሞላ መቅደሳችን
 ዶ/ር ብዕለ ፀጋን ከዳግማዊት ኢትዮጵያ ከዲሲ አስነስቶ
ከዚህ ከበረሃው ገዳም ከሚባለው ከፊኒክስ አምጥቶ
በመንፈሳዊ ትምህርት በቅዳሴው ስርዓት እያገለገለን
ስጋችን ሲታመም የመጀመሪያ እርዳታ ከዲያቆኑ ዶክተር ቶሎ እናገኛለን።

እንዲያው በአጠቃላይ ትልቅ ትንሾቹ
                        ሁላችሁ ዲያቆናት
ለቤቱ የጠራችሁ የእስጢፋኖስ ልጆች
የማነ አንተነህ እንዲሁም ተስፋሁን
ወንድማማቾቹ ነብዩና ብንያም
አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ይባርኳችሁ
ከተኩላ ጠብቆ በተዋህዶ አጽንተቶ
ለበለጠ ክብር እግዚአብሔር ያብቃችሁ።

በስተመጨረሻ ይሄን ላደረገ ለአምላክ ውለታ
አንድ እቅድ አቀድን በቻልነው ችሎታ
የነበረን ድረ ገጽ በደንብ ተጠናክሮ
ሰፊ አገልግሎት እንዲሰጠን ታስቦ
ህዝቡ ስራ ደክሞት ከቤቱ ለቀረው
በተለያየ ምክንያት አልመቻች ላለው
ከቤቱ ውስጥ ሆኖ ወንጌል እንዳይርበው
እለት እለት ቃሉ ውስጡን እንዲያጸናው
ስለ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ መረጃ ድንገት ከፈለጉ
የተለያዩ ስብከቶች በቀላሉ መንገድ በዚያ እንድናገኝ
ከዛሬ ጀምሮ www. Phoenixestipanos በማለት የቤተክርስቲያናችንን አዲሱን ድህረ ገጽ
                                    እባክዎን ይጎብኙት።
 


ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ሌላ የምላችሁ
ይጠቅማል ስትሉ ለቤተክርስቲያናችን
ያላችሁን አምጡ ለድህረ ገጻችን
አምላክ እንዲደሰት በፍቅር ሁኑና
የሰው ሁሉ መክሊት ይለያያልና

ሁሉም በችሎታው ይሳተፍ ይምጣና
ከሩቅም ከቅርብም በዚህ የተገኛችሁ
ሊቃውንት አባቶች ካህናት ሁላችሁ
የሰማዕቱን በዓል ለማክበር ብላችሁ
የግል ዘማሪያን የሰ/ትቤት ጭምር
ምዕመናን ሁላችሁ ከዚህ የተገኛችሁ በዓሉን ለማክበር
ዕድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍስሃ ይስጣችሁ እግዚአብሔር
                                    ወስብሐት ለእግዚአብሔር
            +++ አሜን+++
                                    ምስጢረ ድግሴ
                                                2010 ዓ/ም

 

bottom of page