top of page

ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ሕጻናት ክፍል

 

“ከሕጻናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ።”

ዓላማ

የደብረ መዊዕ ቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ እስጢፋኖስ የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ሕጻናት ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው” ብሎ ያዘዘውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ በፈኒክስ አሪዞና የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝ የሆኑ አዳጊዎችን በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ሃይማኖታቸውን እንዲያውቁና እንዲጠብቁ፣ ቋንቋቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲሁም ባህላቸውን እንዳይረሱ ትምህርት በመስጠት እና የተማሩትን በተግባር እንዲፈጽሙ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። በይበልጥም ክፍሉ ሕጻናት እና አዳጊዎች ልጆቻችን የነገይቱ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢዎች እንዲሆኑ ለማድረግና ይህንንም ዓላማውን ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ ሥራዎችን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል።

የሕጻናት ትምህርት መርሐ ግብር

  • ዘወትር ቅዳሜ ከ4:00pm-6:00pm

  • ዘወትር እሑድ ከቅዳሴ በኋላ

 

የሚሰጡ ትምህርቶች ዝርዝር

  • የአማርኛ ፊደላት ቁጥር፣ ንባብ እና መጻፍ

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ

  • አምስቱ አዕማደ ምሥጢር በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ

  • ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ

  • መዝሙራት 

  • የአብነት ትምህርት በግዕዝ (ጸሎተ ሃይማኖት፣ ውዳሴ ማርያም፣ መልክዐ መልክዕ፣ ሥርዓተ ቅዳሴ፣ ወዘተ ንባብ እና ዜማ)

የሕጻናት ክፍሉ አባላት/መምህራን

የቤተ ክርስቲያናችን ሕጻናት አገልግሎት ክፍል ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ ለማሳካት፣ ልጆቻችንም በማስተማር እና የነገ ተረካቢዎች እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ያለብንን ከፍተኛ ኃላፊነት በጥልቅ የተረዳው ጉዳይ ነው። ስለዚህም ይህንን ሥራ ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚፈጽሙ፣ በመንፈሳዊውም ሆነ ዓለማዊው ትምህርታቸውና ሙያቸው የተመሰከረላቸውን አባላት መርጦ በማገልገል ላይ ይገኛል። እነዚህን መምህራን ወላጆች እንድናውቃቸውና በሙሉ ልብ አምነንባቸው ልጆቻችንን እንዲማሩ እንድናደርግ ይረዳን ዘንድ ከዚህ በታች ስም ዝርዝራቸውን አካትተናል።

  • ዶ/ር ሰላማዊት አሥራት 

  • ወ/ሮ ሚና ብዙአየሁ 

  • ወ/ሮ ንግሥት ቡርጋ 

  • አቶ ዳዊት አዳነ 

  • አቶ ዳንኤል ኃይለ ጊዮርጊስ

  • አቶ እንግዳወርቅ ኃይሌ 

  • ዲ/ን ዶ/ር ብዕለ ጸጋ ጥበቡ 

ጠቃሚ መረጃዎች

  • ጥያቄዎችና አስተያየቶች ካለዎት ወ/ሮ ሚና ብዙአየሁን ወይም አቶ ዳዊት አዳነን ያነጋግሩ።

bottom of page