top of page

ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት

ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት

 

(ሀ) በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተክስቲያን
• ሐዋ 2፡1 ቤተክርስቲያን የተወለደችው በበዓለ ሃምሳ በኢየሩሳሌም ነው:: ከበዓለ ሃምሳ በኋላም በክርስቶስ ያመኑት ወደየሀገራቸው ተመልሰው ክርስትናን አስፋፉ፡፡

• የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዋርያት ይሠራነበርና የአማኞች ቁጥር በየቀኑ ይጨምር ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ብቻ ከ3,000 እስከ 5,000 ደረሰ፡፡  
ሐዋ. 4፡4 "ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፡፡ የወንዶችም ቁጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ፡፡"

• በቀጣይነት የመብዛታቸው ምክንያትም፡- የሚፈጸሙ ተአምራት እና በፍቅርና በጽድቅ የተሞላው የክርስቲያኖች ሕይወት ነበር፡፡
ሐዋ 5፣14 "ሕዝቡ ግን ያከብሩዋቸው ነበር፡፡ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፡፡"
ሐዋ 2፡47፡፡ "እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፡፡ ጌታም የሚድኑትን እለት እለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር፡፡"


(ለ) ከኢየሩሳሌም ውጪ የነበረችው ቤተክርስቲያን

በደማስቆ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የነበረችው የመጀመሪያዋ የክርስቲያኖች ማእከል ደማስቆ ነበረች፡፡

• ቤተ ክርስቲያኒቱ ሳውል በ37 ዓ.ም. ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት የተመሠረተች ናት፡፡በሐዋ 9፡1-9 ፡፡
እንደ ተጻፈው ሳውል ክርስቲያኖችን ሊያሳድድ ከኢየሩሳሌም ወደ ደማስቆ ይሄድ ነበር፡፡


በአንጾኪያ የነበረችው ቤተክርስቲያን
•ሐዋ 11፡19- 21 “በእስጢፋኖስም ላይ በተደረገው መከራ የተበተኑት እስከ ፊንቄ እስከ ቆጵሮስም እስከ አንጾኪያም ድረስ ዞሩ፥ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለአንድስንኳ አይናገሩም ነበር። ከእነርሱ ግን የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የነበሩት አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው የጌታን የኢየሱስን ወንጌል እየሰበኩ ለግሪክ ሰዎች ተናገሩ።  የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ ቍጥራቸውም እጅግ የሚሆን ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ።"

• የክርስቲያን ማኅበርን በአንጾኪያ በተቋቋመበት ወቅት በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሐዋርያት በርናባስን ወደአንጾኪያ ልከው ነበር፡፡ በርናባስም በጣም ውጤታማ የሆነ አገልግሎትን ፈጽሞ ነበር፡፡
“ወሬውም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተክርስቲያን ስለ እነርሱ ተሰማ፥ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፡፡” የሐ. ሥራ 11፡22፡፡

• ሳውል (ቅዱስ ጳውሎስም) በአንጾኪያ ከበርናባስ ጋር ከተገናኘ በኋላ በአንጾኪያ አንድ ዓመት አብረው አገልግለዋል፡፡
“ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።” የሐ. ሥራ 11፡26

በአንጾኪያ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን እንደ ተመሠረተች ብዙ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ፣ ብዙ ብቃትም የነበራቸው ተከታዮችን አፍርታ ነበር፡፡
“በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምኦንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው ።” የሐ. ሥራ 13፡1-3፡፡

• በአንጾኪያ የነበሩ ክርስቲያኖችም ከአይሁድ ተጽእኖ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ነበሩ፤ ክርስቲያን ተብለውም በመጠራት የሁሉም መጠሪያ  ለሆነው ስም ቀዳሚ ሆነዋል፡፡
“ባገኘውም ጊዜ  ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።” የሐ. ሥራ 11፡26፡፡


• ሐዋ. 9፡20 "ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በምኵራቦቹ ሰበከ።"


• ክርስትና ለዓለም የተስፋፋበትን ሁኔታ ለመረዳት ሐዋርያቱን በሚከተለው መንገድ በመክፈል ልንረዳ እንችላለን፡፡


ሥርዓተ አምልኮ በሐዋርያት ቤተክርስቲያን


(ሀ) ቤተ ክርስቲያን
• ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ትምህርትና ሐሳብ የእግዚአብሔር ቤት ናት፡፡
1ኛጢሞ. 3፡15 "ነገር ግን ብዘገይ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነው፡፡" ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት፡፡

• በቤተክርስቲያን በሚፈጽሙ ምሥጢራ ትበረከትና ጸጋ እናገኛለን፤ በዘመነ ሐዋርያት የነበረችው ቤተከርስቲያንም ለምሥጢራት ጥቅም ትኩረት ነበራችው፡፡በሐዋርያት ሥራ ምእ. 9 እና 10 የተጠቀሰውን


(ለ) የጌታ እለት - እሁድ
• ጌታችን ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ስለሆነች የጌታ ቀን ትባላለች፡፡ እሁድ አይሁድ የሚያከብርዋትን ቅዳሜ ተክታለች፡፡

• በመጽሐፍ ቅዱስ እሁድ ክርስቲያኖች ተሰባስበው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉባት መሆኑ ተገልጾዋል፡፡

•ዮሐ 20፡26  "ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቴ ደግመው በውሰጥ የነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፣ በመካከላቸውም ቆሞ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡”
ሐዋ 20፡7 "ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፣ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፣ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ፡፡"


1ኛቆሮ16፡2 "እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ፡፡"

 


(ሐ) ለአምልኮ መሠባሰብ ቦታዎች
• የሥርዓተ አምልኮ መሠባሰቢያቸው በቤቶች ነበር፡፡ ለምሳሌ በበዓለ ኃምሳ በተሰባሰቡበት በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ነበሩ፡፡ ሥራ 2፡1-ፍጻሜ፣ሥራ 12፡12፡፡

ሥርዓቱ
• በቅዱስ ቁርባን ጊዜ ወንጌል በማንበብ ይጀመራል፣ የነቢያት ትንቢት ይነበባል፣ ስብከት ከተሠጠ በኋላ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ጸሎቱም ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች፣ ስለ ሠላም እና የምሥጢራት አፈጻጸም ጸሎት ናቸው፡፡ ሥራ 1፡14፣ 3፡1፣6፡4፣ 12፡5፣ቆላ 1፡9፣ ቀዳ ጢሞ 4፡5፣ ራእ 5፡8፣ 8፡4-5፡፡

አጋፔ "የምእመናን ስብስብ-አንድነት"

• አጋፔ በሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የታወቀነው፡፡ ክርስቲያኖች በአንድነት ተሰባስበው መዝሙር የሚዘምሩበት የሚማሩበትና የሚመገቡበት ነበር፡፡ በመጀመሪያ አጋፔ ከቅዱስ ቁርባን ጋር የሚፈጽሙ ነበሩ፡፡ በኋላ ግን ሁለቱን ሙሉ በሙሉ ለይተዋል፡፡ ቀዳ ቆሮ 11፡1-…፡፡

የመስቀል ምልክት
• የክርስቶስ መስቀል ከመጀመሪያ ጀምሮ ለክርስቲያኖች የክብርና የቅድስና ምልክት ነበር፡፡ በደረታቸው እና በክንዳቸው ይነቀሱትም ነበር፡፡ የመስቀል ምልክት ያደርጉ የነበሩትም የመስቀልን ኃይል ለማግኘት፣ ዲያብሎስን ለማሸነፍ እና በመስቀል የተገለጠውን የጌታችንን ፍቅር ለማስታወስም ነበር፡፡
"የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፣ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና;; " ቀዳቆሮ. 1፡18፣ገላ 6፡14፡፡

bottom of page