ታቦትናጽላት

·

ታቦት የጽላት ማደሪያ ነው፡፡ ዘዳ 40፥20፡፡

ጽላት ደግሞ ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት ነው፡፡ ዘዳ 34፥27-28፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች ዛሬም በሐዲስ ኪዳን አሉ። ሆኖም ግን አሠራሩ ሙሉ በሙሉ በዘጸ 25፥10-18 ያለውን የሙሴን ሕግ የተከተለ አይደለም፡፡ ምክንያቱም፤ 

 

1ኛ፡ ታቦት እንደ ሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡


2ኛ፡-ጽላት ፤ ጽላትም እንደ ሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1 በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ቆላ 2፥17፤ዕብ 10፥1፡፡


እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ የሚል ጥያቄም ሳይነሳ አይቀርም፡፡

የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡


ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል፡፡ ከሌለንም ወርቁ ይቀራል ቀኖና ነውና፡፡


ስለጽላቱም እንደዚሁነው ከቻልን ከከበረ ድንጋይ፣ ከዕብነበረድ መቅረጽ እንችላለን፤ ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን፤ ካልቻን በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን ቀኖና ነውና፡፡

በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛቆሮ 3፥1-3፤በዕብ 8፥8-13፡፡ የእኛ አካልና ልቡና የእርሱ ታቦትና ጽላት አልሆነም ወይ? በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦት ና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ የሚሉ አሉ፡፡ የክርስቲያኖች አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተመቅደስ መሆኑን እናምናለን፡፡ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፤ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደ ባልጀራ ያነጋገረበት፣ የክብሩ ዙፋን ሆኖ ጽላቱ በውስጡ ለታቦቱ ማደሪያ በመሆኑ፤ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኅኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው፡፡ጽላት ከእግዚአብሔር ስለመስጠቱ

 
ዘጸአት 24-12 "እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።"ዘጸ 25:10 "ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።" ዘጸ 25:21 የስርየት መክደኛውንም በታ ቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።

 
ዘጸአት 31-18 "እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።" ዘጸአት 32-15-17 "ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር። ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ። እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ጽላት ተሰብራል ከዚያም በኃላ መልሶ አለሰጠውም ለሚሉ ሙሴ መልሶ እንደ በፊቱ አድርጎ እንዲሰራ እግዚአብሔር ማዘዙን ለማመልከት ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ  ዘጸአት 34:1 "እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደፊተኞች አድርገህ ጥረብ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።" 
ዘጸ 34:28 "በዚያም አርባ ቀንና አርባሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃልኪዳን ቃሎች ጻፈ።" ዘጸ37:1 "ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።" ዘጸ 40:20 "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ዘንድ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታ ቦቱ ላይ አኖረው" 
ዘዳግም 10:1-5 "በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር፦ እንደፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራውውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች እጽፋለሁ፥ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ። ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀንእግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔሰጠኝ። ተመልሼም ከተራራውወረድሁ፥ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖ። 

 

እነዚህ ሁሉ ታቦቶች ከየት መጡ ?

·       

በዘዳ 31፣18፣32፣15፣134፣1-5፡፡2ኛዜና 5፣10 ያሉትን ጥቅሶች በመጥቀስ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ሁለት ጽላቶችን ብቻ ነው፡፡ ነገርግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህን እልፍ አእላፋትጽላቶች ከየት አመጣቻቸው? አራብታችሁ ቅረጹ የሚል አለ ወይ?


መልስ፡- በዘዳ 32፥19፡፡ ስንመለከት እግዚአብሔር ራሱ አዘጋጅቶ ለሙሴ የሰጠውን ሁለቱን ጽላቶች እሥራኤል ጣዖት ሲያመልኩ ስላገኛቸው ሙሴ ተበሳጭቶ ሰብሯቸዋል፡፡ ነገርግን ቸርነቱ ለዘለዓለም የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴ የመጀመሪያዎቹን አስመስሎ እንዲሰራ ነገረው፤ ሙሴም አስመስሎ ሠራ፡፡ ዘዳ 34፥1-5 መሥራት ብቻ ሳይሆን ዐሥሩን የቃልኪዳን ቃላትም በጽላቶቹ ላይ እንዲጽፍ ሙሉ ሥልጣን ከእግዚአብሔር ተሰጠው፡፡ ሙሴም ተፈቅዶለታልና አሥሩን ቃላት በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፡፡ ዘዳ 34፥27-28 ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጽላትንም ሆነ ታቦትን እያስመሰሉ ለመሥራት ሙሉ ሥልጣንን አግኝተናል፡፡ ይህን በተመለከተ አንዳንድ አባቶች እንዲህ ይላሉ፤
‹‹አዳም እንኳን በደለ አዳም ባይበድል ኖሮ አምላክ ሰው ሆኖ በቀራንዮ ስለእኛ የመሰቀሉን፤ ስለኛ የመሞቱን የፍቅር ምስጢር አናውቀውም ነበር፡፡››

እስራኤልም በጥጃ ምስል ጣኦት አምልከው እንኳን በደሉ እሥራኤል ባይበድሉ ሙሴ በእግዚአብሔር የተዘጋጁት ሁለቱ ጽላቶች' የሰው ልጅም እግዚአብሔር የሠራቸውን የፊተኞቹን አስመስሎ ለመሥራት ስልጣን ባልኖረውም ቢሠራም ለምን ሠራህ ለሚለው መረጃ ባላቀረበም ነበር›› ይላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ጽላትን አስመስለን፤ አባዝተን፤ አራብተን ለመሥራት መሠረታችን ሥልጣኑ ለኛ ለልጆቹ የተላለፈልን ከአባታችን ከሙሴ ነው፡፡››

 

ሙሴ የተሰበሩትን አስመስለህ ሁለት ጽላቶች ቅረጽ ከሚል በቀር ጽላቶችን አብዝታችሁ፤ አራብታችሁ ተጠቀሙ የሚል ቀጥተኛ ቃል አምጡ ለሚለው ግን ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የጽላትም ሆነ የቤተመቅደስ ሥርዐት፤ የመስዋዕቱ የዕጣኑ አገልግሎት፤ በኢየሩሳሌም ብቻ ስለነበረና፤ የሌላውም አገር ሕዝብ የሚከተለው የጣዖትን ሥርዓት እንጂ የሙሴን ሥርዐት ባለመሆኑ ጽላቱ ተባዝቶ ተራብቶ ለሌላው አገር ሕዝብ አልተሰጠም፡፡ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ውጭ አልፈቀደም የተቀደሰውን ጣዖታውያኑ አሕዛብ ያረክሱታልና ስለዚህ ስግደቱም የቤተመቅደስ ሥርዐቱም በኢየሩሰሳሌም ብቻ ነበር። /ዮሐ 4፥18-24/ 

በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ አሕዝቦችም ሠሎሞን ያሠራው ታላቁ ቤተመቅደስና ሁለቱ ጽላቶች አንሰውናል፤ በርቀት የምንገኝ እኛ የመንገድ ድካም በዝቶብናልና፡፡ ስለዚህ በያለንበት ቤተመቅደስ ሠርተን ጽላቱን አክብረን መገልገል እንፈልጋለንና ይፈቀድልን ብለው ሙሴም ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ሌላ አልተፈቀደም ብሎ መልስ የሰጠበት ቦታ የለም፡፡ ያም ሆነ ይህ በሐዲስ ኪዳንም በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው፤ ሁለተኛ የድኅነት ልደት ተወልደው የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣን ሰጣቸው። ለክርስቲያኖችም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ እንደሚበዙና በአዲስ ኪዳን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስስም ንጹሕ የሆነውን ቁርባን ከኢየሩሳሌም ውጭ በየቦታው ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡1. ‹‹ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ይከበራልና፤ በየስፍራው ለስሜዕጣን ያጥናሉ፤ ንጹሕንም ቁርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር›› ሚል 1፥11፡፡
2. ‹‹ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎ የለምን? እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ አስተማራቸው›› ማር11፥17፤ኢሳ 56 ፥ 7፤ኤር 7፥11 ፡፡ ይህ ትንቢት በቀጥታ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ቤተመቅደስም ሆነ የዕጣን፤ የቁርባን አገልግሎት እንኳን ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ላሉ አሕዛብ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በቀር ለእስራኤል ጎረቤት አገሮች እንኳ አልተፈቀደምና፡፡ ነቢዩ ሚልክያስ ንጹሕ ዕጣን ያለው በማቴ 2፥11፡፡ ወንጌል እንደተናገረው ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰብአሰገል በቤተልሔም ዋሻ ለክርስቶስ ካቀረቡት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ለክርስቶስ የምናቀርበው ቅዱስ ዕጣን ነው፡፡


ንጹሕ ቁርባን የሚለውንም በማቴ 26፥26፤ ጌታ ኅብስቱን አንሥቶ ነገ የሚቆረሰው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ወይኑንም አንሥቶ ነገ ስለብዙዎች ሀጢአት የሚፈሰው ደሜ ይህነው ብሎ ለሐዋርያት የሰጣቸው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ ንጹሕ የተባለው እርሱ በባሕርዩ ንጹሕ ሆኖ የእኛን የኃጢአት እድፍ ስለሚያነጻ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በኢየሩሳሌም ብቻ መሆን የሚገባቸው ቤተ መቅደሱ፤ ዕጣኑ፣ ቁርባኑ፣ በክርስቶስ ደም በአዲስ ሕይወት፣ በአዲስ ተፈጥሮ፤ በአዲስ ሥርዓት፣ ክርስቲያኖች ለሆንን ለዓለም ሕዝቦች በየሥፍራው (በያለንበት) እንድንጠቀምባቸው ከተፈቀዱልን በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሁለቱ ጽላቶች ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ተባዝተው በዓለምያለን ክርስቲያኖች በያለንበት በየቤተመቅደሳችን ለሥጋውና ለደሙ የክብር ዙፋንነት ብንገለገልባቸውና የአምላካችን የኢየሱስክርስቶስን ስም ብናከብርባቸው ምን የሚጎዳ ነገር ተገኘ? የሚያስደነግጠው ስምኑ ነው? ስህተቱስ የቱ ላይ ነው?

እንዲሁም ዐሠርቱ ትእዛዛት የተጻፉባቸው ሁለቱ ጽላቶች መባዛት መራባት የለባቸውም ከተባለ በጽላቶቹ ላይ የተጻፉት ዐሠርቱ ትእዛዛት መባዛት የለባቸውም፡፡ ከኢየሩሳሌምም መውጣት የለባቸውም ማለት አይደለም? ትእዛዛቱም ተከለከሉ ማለት ነውና፡፡ በጽላቶች ላይ የተጻፉት ትእዛዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ በፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በሚገኙ ክርስቲያኖች እጅ ገብተዋል፡፡ይህም ያስደስታል እንጂ አያሳዝንም፡፡ ይህ ከሆነ ለሥጋውና ለደሙ (ለክርስቶስ) ክብር ሲባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ጽላቶችምን በደል አስከተሉ፥ እግዚአብሔር ለቀደሙ አባቶቻችን በታቦቱ አድሮ የሠራላቸውን ድንቅ ሥራ እያስታወስን እግዚአብሔርን ከማመስገን ውጭ ደግሞም ጌታ ስለጸሎት ሲያስተምረን ‹‹አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ውስጥ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን›› በሉ ብሏል፡፡በዚህ መሠረት በዮሐንስ ራዕይ 11፥19 ላይ ታቦቱን በሰማይ አሳይቶናል፡፡ ስለዚህ የሙሴ የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰማይ እንዲገኝ፤ በሰማይ እንዲሆን፤ በሰማይ እንዲታይ ፈቃዱ ከሆነ፤ በምድርም እንዲሆን ፈቃድህ ይሁን ብለን ብንጠቀምበት ስህተቱምን ይሆን?

 
 

ታቦቱ በቤተ ክርስትያን (በቅዱሳን ስም ይሰየማል?)

 

አዲስ ቤተክርስቲያን በሚሰራበት ጊዜ ከእጽ ወይም ከእብነበረድ ተቀርጾ በላዩ የጌታችን የኢየሱስክርስቶስ ስም (አልፋ እና ኦሜጋ ኢየሱስክርስቶስ ተብሎ ይጻፍበታል) የመጀመሪያውና የመጨረሻው ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ከተጻፈበት በኋላ በኤፒስቆጶሱ እጅ ተባርኮና ሜሮን ተቀብቶ በመንበሩ ይሰየማል (ይቀመጣል) ፡፡በቅዳሴም ጊዜ ሕብስቱና ወይኑ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ቄሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ሕብስቱን ሥጋ መለኮት፣ ወይኑን ደመ መለኮት ወደ መሆን የሚለውጠው በዚህ በታ ቦቱ ላይ ነው፡፡ 

የኦሪት ጽላት እግዚብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ አሁን ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፡፡ ሥጋዬን ብሉ ደሜንም ጠጡ እያለ ያመኑትን ሁሉ የሚጠራበት የምሕረትምሥዋዕ (መሠዊ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ስለዚህ ነው፡፡

ለምን በቅዱሳን ስም ይሰየማል?


መሠየሙ በትንቢተ ኢሳይያስ 56፥46 በተገለጸው መሠረት የእግዚአብሔርን ሰንበቱን ለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘውንም ለሚመርጡ ቃል ኪዳኑንም ለሚይዙ ጃንደረቦች (ስለእግዚአብሔር መንግሥት ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ቅዱሳን) ማቴ 19፥12 በእግዚአብሔር ቤትና በቅጥሩ የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሚደረግላቸው የተገለጠበ መሆኑ ይህን አብነት በማድረግ ጌታሥጋው፣ ደሙ የሚከብርበት ሆኖ ለቅዱሳኑም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፡፡ /መዝ 111፥7/ እንዲሁም የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነውና ምሳ 10፥7፡፡ በዚህ ምክንያት እንጂ በታ ቦታቱ የሚከብረው መድኃኒተ ዓለም ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ስግደት ለምን ይደረግለታል?


ከላይ እንደ ተገለጸው ታቦቱ ላይ ያለው ስም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስምነው (አልፋ ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስ) ለጌታችን ስም ደግሞ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‹‹ይህም በሰማይና በምድር በቀላያትና ከምድርም በታች ያለጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው። አንደበትም ሁሉኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብክብር ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው›› ፊልጵ 2፥10-11፡፡

 

በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መንበርከክ እና መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ዘጸአት 24-12 "እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይ ምጽላት እሰጥሃለሁ አለው።" ዘጸ 25:10  "ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።" ዘጸ 25:21 የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህንም ስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ። 

 

ዘጸአት 31-18 "እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።"

ዘጸአት 32-15-17 "ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር። ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።

እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ጽላት ተሰብራል ከዚያም በኃላ መልሶ አለሰጠውም ለሚሉ ሙሴ መልሶ እንደበፊቱ አድርጎ እንዲሰራ እግዚአብሔር ማዘዙን ለማመልከት ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ  ዘጸአት 34:1 "እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደፊተኞች አድርገህ ጥረብ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።" 
ዘጸ 34:28  "በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃልኪዳን ቃሎች ጻፈ።" 
ዘጸ 37:1  "ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።" 


ዘጸ 40:20  "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ዘንድ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው"

ዘዳግም 10:1-5  "በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር፦ እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች እጽፋለሁ፥ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ። ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ።"

ለታቦት ሊደረግ የሚገባ ክብር 

ታቦት የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫ ዙፋን እንደሆነ ሁሉ ይከብር ዘንድ ግድ ነው ይህንንም በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃነት እናያለን:: 
1ኛ ሳሙ 4:5  "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።" 
ምዕመናን ታቦት በሚወጣበት ጊዜ እልልታ የሚያቀርቡት የሚያጨበጭቡት ይህንን መሰረት አድርገው ነው::

2ኛ ሳሙ 6:16-23  "የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፥ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘፍን አየች በልብዋም ናቀችው። የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም።" (የዛሬዎቹ መናፍቃን የሜልኮል ዘር ናቸው)

ኢያሱ 3:3  "ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።" 


ኢያ 7:6  "ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ይህ ሁሉ ሥራዓት ዛሬም በጥንታዊት ሐዋርያት ቤተክርስቲያን ይጠበቃል:: 


ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች 

ዘኁ 7:89  "ሙሴም ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር እርሱም ይናገረው ነበር።" 
ኢያ 6:6 "የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ። የቃልኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው።"
1ኛዜና 13:7  "የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።" 
1ኛዜና 15:1  "ዳዊትም በከተማው ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፥ ድንኳንም ተከለለት።" 
2ኛዜና 6:11  "እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጸመ እግዚአብሔርም ተስፋ እንደሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፥ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፥ ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ። ከእስራኤልም ልጆች ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ያለበትን ታቦት በዚያው ውስጥ አኖርሁ።" 
2ኛዜና 8:11  "ሰሎሞንም። የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።"

መዝ 131:8  "አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥አንተና የመቅደስህ ታቦት።" 
ማቴዎስ 5:17  "እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

ራእይ 11፥19  "በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።"

4901 W Indian School Rd

Phoenix, AZ 85031

(602) 328-0992

  • Facebook Social Icon