top of page

በዓላት

·        በዓል ማለት የተቀደሰ የተከበረ ልዩ ክቡር ቀን ማለት ነው:: በዓላት በልማድ የሚከበሩ ወይንም ስራን ላለመስራት ተብሎ የተፈጠሩ አይደሉም:: የበዓላት ሁሉ መገኛ ምንጫቸው ሃይማኖት ነው:: በብሉይ ኪዳን የሚከበሩ ብዙ ዓይነት በዓላት ነበሩ:: የበዓላት ሁሉ መሰረት ግን ቀዳሚት ሰንበት ናት:: ሰንበት ማለት ዕረፍት ማለት ነው::

ዘፍ 2:2 "እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። " በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ቅዳሜና እሁድ ነው:: ሰንበተ ክርስቲያን እሁድ ጌታ ፍጥረትን መፍጠር የጀመረበት : የተጸነሰበት : ከሙታን ተለይቶ የተነሳ በትናትና ይህች ዕለት ትከብራለች::
ዘጸ 16:23 20:8 "እርሱም፦እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው።ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው  የምትጋግሩት ንጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው። " 
መዝ 41:4 "ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።" 
መዝ 75:10 "ሰው በፈቃዱ ያመሰግንሃልና፥ ከሕሊናቸው ትርፍም በዓልህን ያደርጋሉ።" 
ዮሐ 10:22 "በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ" 
ሐዋ 20:7 "ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን ፥ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ።" 
1ኛቆሮ 16:2 "እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረበ ቤቱ ያስቀምጥ።" 
የጌታ ዘጠኝ ዓበይት በዓለትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻቸው
1-ብስራትሉቃ 1:26
2-ልደትሉቃ 2:7
3-ጥምቀትማቴ 3:13 ሉቃ 3:21
4-ደብረታቦርማቴ 17:1 ማር 9:21 ሉቃ 9:28
5-ሆሳዕናማቴ 21:1
6-ስቅለትሉቃ 23:33
7-ትንሳኤሉቃ 24:5
8-ዕርገትሉቃ 24:50
9-ጰራቅሊጦስሐዋ 2:4
ዘጠኙየጌታንኡሳንበዓላት
1-መስቀልማቴ 27:1 1ኛቆሮ 1:18
2-ስብከትዮሐ 1:44 ዕብ 11:1
3-ብርሃንመዝሙር 42:3 ኢሳ 9:2 ዮሐ 8:12
4-ኖላዊመዝ 22:1 ዮሐ 10:1-22 1ኛጴጥ 2:25
5-ግዝረትዘሌ 12:3 ሉቃ 2:21
6-ልደትስምዖንሉቃ 2:25
7-ቃናዘገሊላዮሐ 2:1
8-ደብረዘይትማቴ 24

Anchor 1

                                     

 

 

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሚስጥረ ጥምቀት አፈጻጸም ብርቱ ጥንቃቄ ታደርጋለች።ሰው ሁሉ በጥምቀት አማካኝነት የሚሰጠውን ጸጋ እንዲያገኝ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ተፈጽማለች። ሰዎች ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ በማለት ሕፃናትን እንዲጠመቁ ታስተምራለች ታጠምቃለችም። ሕፃናትን የምታጠምቀው በቅዱሳት መጻሕፍት በቅዱሳን አበው ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ነው።ሕፃናትን የምታጠምቀው ከቅዱሳት መጻሕፍት በተረዳችው መሠረት እንደሆነ ከዚህቀ ጥለን ለማየት እንሞክራለን። 

መጽሐፈ ኩፋሌ 4:9 "ከተፈጠረባት ምድር ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኃላ ይገዛትም ይጠብቃትም ዘንድ ወደገነት አስገባው። ሚስቱንም በሰማንያ ቀን አስገባት።" 
ይላልና ለአዳምና ሔዋን ንፁሕ ጠባይዕ ሳያድፍባቸው ከመንፈስቅዱስ የጸጋ ልጅነት ተቀብለው በ40 ና በ80  ቀን ገነት እንደ ገቡ ዛሬም ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር መጀመሪያ በሠራው ሥርዓት መሠረት በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት የተወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ሕፃናት ወንዶችን በ40 ቀን ሕፃናት ሴቶችን በ80 ቀን ዕድሜያቸው ታጠምቃለች። 

ሀ. ሕፃናት የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ ወላጆቻቸው ና ቤተክርስቲያን የሚሹት ነው፡፡ 

የሐ.3÷5"ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፡፡ 
ስለዚህ ሕፃናት በወላጆቻቸው እምነት የተነሣ የወላጆቻቸውን እምነት የእነርሱ እምነት በማድረግገና በሕፃንነት ጊዜያቸው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጭ እንዳይሆኑ ታጠምቃቸዋለች፡፡ ዳሩግን ሳይጠመቁ ቢሞቱ ጌታ እንደተናገረው መንግስተ ሰማይን አያዩአትም፡፡እንደ ጌታ ትምህርት የምንሄድ ከሆነ #ሰው ብሎ ባጠቃላይ ሕፃናትን አዋቂዎችን ሁሉ ጨምሮ ተናገረ እንጂ ከሕፃናት በስተቀር አላለም፡፡ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፡፡ 

ለ. ሕፃናት በመጠመቃቸው የቤተክርስቲያን አባል ስለሚሆኑ የእግዚአብሔር ጸጋ ተከፋዮች ይሆናሉ፡፡ ገና ከሕፃንነታቸው ጀምሮ የቤተክርስቲያንን ሕይወት ይለማመዳሉ፡፡ በዚህ ፈንታ ከሕፃንነታቸው ጊዜ ጀምረው ከእግዚአብሔር ጸጋ ተራቁተው የሚያድጉ ከሆነ ለመጥፎ ሕይወት ይዳረጋሉ፡፡ 

ሐ. ለሕፃናት በሚደረግ ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ አይቃወምም እንደውም ይደግፋል፡፡ 

ማር 10:14 "ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሉአቸው 
እንዲሁም ጌታችን  ‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል››  ሲል በዚያን ዘመን ገና ወንጌል መስበክ በጀመረበት ላሉት ሰዎች የተነገረ ሲሆን ከክህደታቸውና ከጥርጥራቸው ተመልሰው የሚመጡ ሁሉ አምነው መጠመቅ እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ሕፃናት የእግዚአብሔር ልጆች ሊሆኑ እንደሚገባ ጌታችን ሲገልጽ 

ማቴ.19÷14‹‹ሕፃናት ወደ እኔይመጡ ዘንድ ተውአቸው አትከልክሏቸው መንግሥተ ሰማያት እንደ እነርሱ ላሉት ናትና›› ብሏል፡፡ 
በዚህ የጌታ ትምህርት መሠረት ቤተክርስቲያንም የመሪዋንና የመሥራችዋን የክርስቶስን ቃል መርሕ በማድረግ ወላጆቻቸው ታቅፈው ወደቤተክርስቲያን ይዘው በመምጣት ተጠምቀው የእግዚአብሔር ልጆች የቤተክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ ሲያደርጉ እርሷ ከልካይ አትሆንም ፡፡ ጌታ ተውአቸው ይምጡ ልጅነትን ፣ጸጋን ፣በረከትን ያግኙ ብሏልና፡፡ 
ሕፃናት ንጹሐነ አእምሮ መሆናቸውን ጌታ ሲያስተምር እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ መንግሥተ ሰማይ አትገቡም ብሏል፡፡ 

መ. መጽሐፍ ቅዱስ ሕፃናት መጠመቃቸውን ያስተምረናል፤ 


1. ሐዋ.16÷33 "በእሥር ቤቱ በተደረገው ተአምር የተደነቀውና ወደ ክርስትና እምነት የተሳበው የወኀኒ ጠባቂ ጳውሎስ ና ሲላስ ካስተማሩት ና ካሳመኑት በኋላ ከነቤተሰቡ መጠመቁ ተገልጾአል፡፡ እግዲህ የተሰበከው ና ያመነው የወኀኒ ጠባቂው ሲሆን የተጠመቁት ግን ሕፃናትን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ ነው፡፡ " 

2. ሐዋ.16÷15 "ልብዋን ጌታ የከፈተላትና ቃሉን አድምጣ ሕይወትዋን ለክርስቶስ የሰጠችው ልድያ ባመነች ጊዜ የተጠመቀችው ብቻዋን ሳይሆን ከመላው ቤተሰብዋ ጋር ነው፡፡ከቤተሰቡ መካከል ሕፃናት መኖራቸው የማይቀር ነው፡፡ 

3. 1ቆሮ.1÷16 "ቅዱስ ጳውሎስ የእስጢፋኖስንም ቤተሰቦች ደግሞ አጥምቄያለሁ በማለት የእስጢፋኖስን መላ ቤተሰብ ማጥመቁን ገልኦአል፡፡ እነዚህ የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች ሁሉ ትላልቆች ብቻ ናቸውን? ሕፃናት የሉበትም ይሆን? " 

4. ሐዋ.ሥራ 2 ላይ እንደተገለጸው በበዓለ ሃምሳ ከ3ዐዐዐ ያላነሱ ሰዎች በጴጥሮስ ተሰበኩ፡፡ ከእነዚያ ውስጥ ብዙዎቹ መጠመቃቸው ተገልጿል፡፡ የተጠመቁት ግን ዐዋቂዎች ብቻ መሆናቸውን የሚገልጽ ቃል የለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሕፃናትን ጥምቀት የሚነቅፍ ባንዱም ክፍል ተጽፎ አናገኝም፡፡ እስከ አሁን እንደተገለጸው መጽሐፍ ቅዱስ የሕፃናትን ጥምቀት ያልነቀፈ ሲሆን በብሉይ ኪዳን የጥምቀት ምሳሌ የነበሩትን ስንመለከት ይበልጥ የሕፃናትን ጥምቀት ትክክለኛነት ያረጋግጡልናል፡፡ 

ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነው ፡፡ ሕፃናት በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ይገረዙ ነበር (ዘፍ. 17÷12)፡፡ እንግዲህ ሕፃናቱ የሚገረዙት በወላጆቻቸው እምነት እንጂ እነርሱ ዐውቀው ግረዙን ብለው አይደለም፡፡ የእሥራኤል ቀይ ባሕርን ማቋረጥ የጥምቀት ምሳሌ መሆኑ በ1 ቆሮ.10÷2 የተገለጸ ሲሆን ባሕሩን ያቋረጡት ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናትም ጭም ርናቸው፡፡ከባርነት ከፈርዖን አገዛዝ ነፃ የወጡት ሕፃናቱም ጭምር ናቸው፡፡ እሥራኤል ከበኲረ ሞት የዳኑበት የአንድ ዓመት ጠቦት በግ ደግሞ ምሳሌነቱየ ጌታ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በዚያን ጊዜ በበጉ ደም አማካኝነት ከሞት የዳኑት የታዘዙትን እሺ ብለው የፈጸሙት ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ የእነርሱ ልጆችም ጭምር ናቸው፡፡ እንግዲህ በወላጆቻቸው እምነት ሕፃናቱ መዳናቸውን ልናስተውል ይገባናል፡፡ ስለዚህ ሕፃናት በአእምሮ ባልበሰሉበትና ስለጥምቀታቸው አምነው ተቀብያዋለሁ ሳይሉ የሚደረገው ጥምቀት እውነተኛ ጥምቀት አይደለም የሚሉ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከላይ እንደተገለጸው ሁሉ መሳሳታቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ይመርጣል እንጂ ሰው እግዚአብሔርን አይመርጥም፡፡ ራሱ ባለቤቱ እንዳስተማረው ሁሉ "እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም"" ብሏል (ዮሐ.15÷16)፡፡ድኀነት በእግዚአብሔር ቸርነት የሚገኝ እንጂ በሰው ትምህርትና ዕውቀት የሚሸመት ወይም የሚገበይ ዕቃ አይደለም፡፡ስለሆነም ቤተክርስቲያናችን ሕፃናትን ማጥመቋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ና ከቀደሙት አበው ባገኘችው ትምህርት መሠረት ነው፡፡

Anchor 2

የሕፃናት /የ40 ቀንናየ80 ቀን/ ጥምቀት

ዕጣን

 

ዕጣን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውላል:: ሃያ አራቱ ካህነተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለዓለም ድኅነት የሚለምኑበት ነው:: በቤተ ክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት: በነግህ ጊዜ: በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናውን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል::

ስለ ዕጣን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ

ዘጸ 30:1 "የዕጣን መሠዊያውን ሥራ ከግራር እንጨት አድርገው።" 
ዘጸ 30:34  "እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን።"

ዘጸ 30፥35 በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው።

ዘጸ 40:5  ለዕጣንም የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፥ በማደሪያውም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ።

ዘጸ 40:27 የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ዐጠነበት።

ዘሌ 10:1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ።

ዘሌ 16:12  በእግዚአብሔርም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶጥናውን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ ዕጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።

ዘኍ16፥7  ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ እጅግ አብዝታችኋል ብሎ ተናገራቸው።

ዘዳ 33፥10 ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ።

2ኛዜና 26:16  ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ ወደ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ።

መዝ 140:2  "ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።"

ሚልክ 1:11  ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ 

ማቴ 2:11  "ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።" 

ሉቃ 1:10 "በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።" 

ራእ 5:8  "መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።

ራእ 8:3  ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።

Anchor 3

ሥዕል

 

ሥዕል እንደ ታቦት በኦርየንታል ኦ\ተ\ቤተክርስቲያናት ያለና የሚሰራበት። ስዕል እግዚአብሔር ጋር የተያያዘና በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን የሚሰራበት ነው ስዕል በእግዚአብሔር ፊት የተሰጠ ሕግ ነው። ይኽውም ለሙሴ በታቦተ ሕጉ በጽላት ኪዳኑ ላይ ስዕለ ኪሩብን እንዲስል ታዞ ነበር። በብሉይ ኪዳን የመጀመሪያው ሰዓሊ ሙሴ ነው። ሰሎሞንም የመጀመሪያው ቤተመቅደስ በሠራ ጉዜ ስዕለ ኪሩብን ስሎል። 

ዘጸ 25:19-20  "ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ። ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደስርየት መክደኛው ይመለከታሉ።

ዘጸ 37:7  "ሁለት ኪሩቤልንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠራ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን አደረጋቸው። ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርጎ በአንድ ላይ ሠራቸው። ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ሆኑ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ተያዩ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ተመለከቱ።

1ኛ ነገስት 6:23- 28  "በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ። የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ፥ የኪሩብም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ አሥር ክንድ ነበረ። ሁለተኛውም ኪሩብ አሥር ክንድ ነበረ ሁለቱም ኪሩቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበረ። የአንዱ ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበረ፥ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ። ኪሩቤልንም በውስጠኛው ቤት አኖራቸው የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ተዘርግተው ነበር የአንዱም ኪሩብ ክንፍ አንደኛውን ግንብ ይነካ ነበር፥ የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ ሁለተኛውን ግንብ ይነካ ነበር የሁለቱም ክንፎች በቤቱ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው።

1ኛነገስት 6፥29 " በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ።"

1ኛ ዜና 3፥5  ታላቁንም ቤት በጥድ እንጨት ከደነው፥ በጥሩም ወርቅ ለበጠው የዘንባባና የሰንሰለት አምሳል ቀረጸበት።

ሕዝቅኤል 4:1  አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት የኢየሩሳሌ ምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት፥

መሣ 17፥3  እናቱም። ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ አለችው። አንዱን ሺህ አንዱን መቶ ብርም መለሰላት እናቱም። ይህን ብር የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ አሁንም ለአንተ እመልሰዋለሁ አለች። ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወስዳ ለአንጥረኛ ሰጠችው፥ እርሱም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አደረገው። ያም በሚካ ቤት ነበረ። ሰውዮውም ሚካ የአምላክ ቤት ነበረው ኤፉድና ተራፊም አደረገ፥ ከልጆቹም አንዱን ቀደሰው፥ ካህንም ሆነለት።

Anchor 4

የዜማ ዕቃ በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ

 

መጽሐፍ ቅዱስ እና ማህሌይ ቅዱስ ያሬድ እንዳሳየን ሦስቱ የዜማ ሥልቶች ግዕዝ: ዕዝልና አራራይን የዜማ ዕቃ በሆኑት በከበሮ በገና በጽናጽል በመሰንቆ በመለከት በእምቢልታ የመሳሰሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስ  ቀደምት አባቶቻችን አምላካቸውን ሲያመሰግኑበት በነበረው መሣሪያ እነሱን መሰረት አድርገን አምላካችንን እናመሰግንበታለን። አለም በሚጨፍርበትና ሃጥያት በሚሰራበትና ዘፈን በመሰለ ዜማና በዘመናዊ የዳንኪራ መሣሪያ  ልንጠቀም አይገባም:: ምክንንያቱ መጽሐፍ እንዲህ ብሎናልና  ሮሜ 12:2 "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።"

 

የዜማ ዕቃ በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ

መዝ 150:3-6  "እግዚአብሔርን... በመለከት ድምፅ አመስግኑት በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት በከበሮ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።

ራዕ 15:2  "በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ። ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ፥የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና ፥የጽድቅም ሥራህ ስለተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።" 
1ኛ ሳሙ 16:2 3 "እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉመንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር።" 

1ኛ ዜና 15:16  "ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆች ተናገረ።"

2ኛ ሳሙ 6:5  "ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽል በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።" 

2ኛ ዜና 20:28 "በበገናም በመሰንቆም በመለከትም ወደኢየሩሳሌም ወደእግዚአብሔርም ቤት ገቡ።"

1ኛ ዜና 15:28  "እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆእያሉ ቀን ደመለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃልኪዳን ታቦት አመጡ።" 

ዘፍ 4:21  "የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።" 

ዘጸ 15:20 " የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዘፈን በኋላዋ ወጡ።"

መዝ 33:2  "እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።"

1ኛ ሳሙ 18:6  "እንዲህም ሆነ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።" 

1ኛ ዜና 13:8  "ዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።"

2ኛ ዜና 5:12  "መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር።"

ኢዮ 21:12  "ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል።" 

መዝ 91:3  "አሥር አውታር ባለው በበገና ፥ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።"

ማቴ 24:31  "መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።"

Anchor 5

ጃንጥላ

ጃንጥላ በቤተክርስቲያን በቅዳሴ ጊዜ፥ ወንጌል ሲነበብ፥ ታቦት ሕግ ሲወጣ፥ በልዩ ልዩ አገልግሎት ጊዜ ጃንጥላ ወጥቶ ይዘረጋል። ከተለያዩ ከሚያምሩና ከሚያብረቀርቁ ጨርቅ የሚሰራው ጃንጥላ የመውጣቱና የመጋረዱ ምሳሌ ሊቀነቢያት ሙሴ ጽላተ ኪዳኑን ሲቀበል በደብረሲና የጋረደው ደመና ምሳሌ ነው።


"ሙሴም ወደ ተራራ ወጣ፥ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው። " ዘጸ 24:15
"ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር።" ዘኁ 9:17 "ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀንቀን በላያቸው ነበረ።" ዘኁ 10:34 
"በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።" ማቴ 17:2 
"ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው ፤ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።" ሉቃ 9:34

Anchor 6

ልሳን

 

በዚህ ጽሑፍ መሠረት ልሳን ማለት ቋንቋ ማለት ነው። ልሳን ቁጥር ስፍር ከሌላቸው መንፈስ ቅዱስ ክፍሎ ለክርስቲያኖች ከሚሰጣቸው ስጦታዎች አንዱ ነው። በልሳን መናገር ማለት የሰው ልጆች በሚሰሙትና በሚናገሩት ቋንቋ መናገር ማለት ነው። እንዲሁም በአዲስ ልሳን መናገር ማለት በአዲስ ቋንቋ መናገር ማለት ነው ወይም በአዲስ ቋንቋ መናገር ማለትም ተወልደው ባላደጉበት ወጥተው ወርደው ባልተማሩ ቤት ቋንቋ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት መናገር ማለት ነው።

 

ሐዋ 2:4  "በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።...ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?"

ማር16:17  "ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ" 

1ኛቆሮ 12:10  "ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤"

እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ በሌላ ልሳን መናገር ማለት በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የሰውልጆች በሚሰሙበትና በሚናገሩበት ልዩልዩ ቋንቋ መናገር ማለት እንጂ ሰዎች ሊሰሙት በማይችሉት ወይም ትርጉም በሌለው ቋንቋ መናገር ማለት አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ


1ኛቆሮ 14:39  "ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች (በልዩ ልዩ ቋንቋ) ከመናገርም አትከልክሉ፤ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።"

በልሳን (በልዩ ልዩ ቋንቋ) የመናገር ጸጋ የተሰጠው ሰው በጉባኤ መካከል በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገር ከሆነ በጉባኤው የተሰበሰቡ ሰዎች በሚሰሙበት የወል ቋንቋ መተርጎም እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ያዛል።

1ኛ ቆሮ 14:13  "ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።"
1ኛቆሮ 14:27  "በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤ የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበል።

 

ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ስለ ልሳን ብዙ ከተናገረ በኃላ በእውነቱ ላመኑ ክርስቲያኖች የልሳን ወይም የቋንቋ ጋጋታ ምንም እንደማይጠቅም እንዲህ ሲል ተናገረ 1ኛቆሮ 14:22  "በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም፥ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።"

Anchor 7

መብራት (ጧፍ፣ሻማ)

 

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ በቅዳሴ በማህሌት በሰዓታት አገልግሎት ጊዜ፥ በስዕላት ፊት፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ሲነበቡ መብራት (ጧፍ፣ሻማ) የሚበራው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ በመሆኑና ሰማያዊ ምሳሌ ስላለው ነው። ብርሃኑ ብርሃናውያን (ሰማያውያን) ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ጋር ለመሆናቸው ምሳሌ ነው። ብርሃን ጨለማን እንደሚያስወግድልን ሁሉ እኛም ጭንቀትን፣ መከራን፣ ፍርሃትን እናስወግድበታለን። ሻማው (ጧፉ) ሲነድ እየቀለጠ እንደሆነ ሁሉ ሰማዕታትም ስለእምነታቸው ክብር ሲሉ መስዋታቸውን፤ የወንጌል ፋና የደህንነት ብርሃን ለመሆናቸው ምሳሌ ነው።

 

"መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።"  ማቴ 5:15 
"በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።" ማቴ 25:1 
"ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን" ሉቃ 12:35 
"እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፥ እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስሊላችሁ ወደዳችሁ።" ዮሐ 5:35 
"ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።"  ዮሐ 8:12 "ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።"  2ኛቆሮ 11:14  "በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።" ራእይ 1:20 
ልዑለ እግዚኣብሔር በደብተራ ኦሪት ውስጥ ዘወትር መብራት እንዲበራ አዝዞ ነበር።

 

"መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ መቅረዙ ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀጠቀጠ ሥራ ይደረግጽዋዎቹም ጕብጕቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።" ዘጸ 25:31 37:17  "በቅድስተ ቅዱሳኑም ፊት እንደ ሥርዓታቸው ያበሩ ዘንድ መቅረዞችንና ቀን ዲሎቻቸውን ከጥሩ ወርቅ ሠራ።" 2ኛዜና 4:20 በዘመነ ሐዋርያትም ቢሆን ክፍ ብሎ በሠገነት ላይ የሚበራ መብራት ነበር። "ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ።" ሐዋ 20:8  እኛም ይህን ትውፊት የተቀበልነው ከአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ነው።

Anchor 8

ምጽዋት

 

ሰው ወጥቶ ወርዶ ደክሞ ካገኘው ላይ የሚያደርገው በጎ ስጦታ ነው:: ምጽዋት ብልና ዝገት በማያበላሸው ሌቦችም በማይሰርቁት ስፍራ በሰማይ መዝገብ ማከማቸት ነው:: ምጽዋት ሲሰጡ ብድራትን ሁሉ የሚከፍል እግዚአብሔር መሆኑን አምነን ሊሆን ይገባል:: 2ኛቆሮ 9:6 "ይህንም እላለሁ። በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።" ምሳሌ 19:17 "ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።" 

ሉቃ 14:12 "የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።" 

ሮሜ 12:8 "የሚመክርም ቢሆን በመምከሩይት ጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።"  ሲራክ 3:29 4:1 " ሲራክ 7:33 " 
ሲራክ 29:11 " ምጽዋት ሁሉም በአቅሙ ሊፈጽመው የሚገባ በጎ ተግባር ነው::
ማር 12:41 "ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር" በእምነት የሚፈጽሙት ምጽዋት ሰማያዊ ዋጋ ያለውና የተትረፈረፈ የእግዚአብሔርን በረከት የሚያስገኝ ነው::  ምሳሌ 11:24 "ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም ያለቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።" 

ምሳሌ 28:27 "ለድሀ የሚሰጥ አያጣም ዓይኖቹን የሚጨፍንግን እጅግ ይረገማል።" 2ኛነገ 12:5 "ዮአስም ካህናቱን። ወደእግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለነፍሱም ዋጋ የሚቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደእግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉ፥ ካህናቱ እያንዳንዱ ሰው ከሚያመጣው ይውሰዱ በመቅደስም ውስጥ የተናዱትን ይጠግኑበት አላቸው።"  ሐዋ 10:4 "እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታሆይ፥ ምንድርነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።" 

ማቴ 25:34 "ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥" መዝ 40:1 "ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።" 

ዳን 4:27 "ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት አስቀር።" ሲራክ 29:1-9 ሲራክ 7:10 ሲራክ 3:28 " ሲራክ 16:14 "

Anchor 9

ስግደት 

 

ስግደት በሁለት ይከፈላል እነዚህም የባህርይና የፀጋ ተብለው ይከፈላሉ። የባህርይ ወይም የአምልኮት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ሲሆን ፈጥረህናል ትገዛናለህ ለወደፊቱም ተስፋ መንግስተ ሰማይን ታወርስና ለህብለን የምንሰግድለት ነው። 
የፀጋ ወይም የአክብሮት፥ ለእመቤታችን ለቅዱሳን ለጻድቃን፥ ለመላእክት ሁሉ እግዚአብሔር መርጦአቸዋል አክብሮአችሁማል፥ እኛም እናከብራችሁለን ብለን የምናቀርበው ነው::  ለቤተክርስቲያን ወይም ለታቦት መስገድ ተገቢ ስለመሆኑ  ዘፀ 33:10  "ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።"

 

ኢያሱ 7:6  "ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።"  2ኛሳሙ 12:20 " ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ።"

 

መዝ 5:7  "እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።" መዝ 95:9  "በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ።"  መዝ 131:7  "ወደማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።"

 

መዝ 137:  "ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለምሕረትህና ስለእውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ" 
መዝ 28:2  "የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።"  ሕዝ 46:1  "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦....አለቃውም በስተውጭ ባለው በር በደጀሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ" 

ለመላዕክት የፀጋ ስግደት እንደሚገባ

 

ዘፍ 19:1-2  "ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም በሰዶምበር ተቀምጦ ነበር። ሎጥምባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ " 


ዘኁ 22:31  "እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።"


ኢያሱ 5:13  "እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድርነው? አለው።"



1ኛዜና 21:16  "ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፉ።"



ዳን 8:15  "ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ። እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደሆነ አስተውልአለኝ። 

መሳፍ 13:20  "ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ።"



ለቅዱሳን መስገድ ተገቢ ስለመሆኑ

 

1ኛሳሙ 28:14  "ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጐነበሰ፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣ።"



2ኛነገ 2:15  "ከኢያሪኮም መጥተው በአንጻሩ የነበሩት የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ። የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎ አል አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ ወደ ምድር ተደፉ።"


1ኛዜና 21:21  "ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ተመልክቶ ዳዊትን አየ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፋ።"


ዳን 2:46  "የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆርበግምባሩተደፍቶለዳንኤልሰገደለት፥"


2ኛሳሙ 1:1 "በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሳኦል ሰፈር አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ።"

 
ዘፍ 33:1-8  "ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ፥ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው፥.. .ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞ ምልያና ልጆችዋ ቀርበው ሰገዱ ከዚያም በኋላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ።"


ሐዋ 10:25  "ጴጥሮስም በገባጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደ ቀና ሰገደለት።"


ራዕ 3:9 " እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድነን ከሚሉ ነገርግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊትይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደወደድሁህያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።"

Anchor 10

ስእለት

 

ስእለት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሰው በፈቃዱ ለመስጠት ቃልየሚገባው ነገር ነው:: ሰው ራሱን ከችግር ከመከራ ለማራቅ ለእግዚአብሔር ይሳላል ሆኖም የምንሳለውን ማወቅ አለብን ነገርግን ተስለን ከሆነ ከመፈጸም አንሽሽ፥ ሰውስ እለቱን ባይፈጽም ኃጢአት ነውና:: ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ዕጣን ዘቢብ ጥላ ጣፍና የመሳሰሉትን ብንሳል ጥሩ ነው:: እንዲሁም በጎ ሥራ ለመፈጸም እንደ ዝክር ጸበል ጻዲቅ ነዳያንን መመገብ የመሳሰሉት ያጸድቁናል::

 

ስእለትን በተመለከተ ማስረጃ


ዘፍ 28:20-22 " ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ። " 

ዘኁ 21:2 " እስራኤልም ለእግዚአብሔር፦ እነዚህን አሳልፈህ በእጄ ብትሰጣቸው ከተሞቻቸውን እርም ብዬ አጠፋለሁ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ " ዘዳ 23:21-23 " ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘገይ። ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም። በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።

 " 

መሣፍ 11:30  "ዮፍታሔም። በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናልብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። ዮፍታሔም ሊዋጋቸው ወደ አሞን ልጆች አለፈ፥ እግዚአብሔርም በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው።

" 1ኛሳሙ 1:11  "አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። " 

 

መዝ 49:14 " ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ "


መዝ 75:11  "ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ በዙሪያው ያሉ ሁሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ። "


ምሳ 20:25  "ሰው በችኰላ። ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው። "


መክ 5;4  "ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው። "


ዮና 2:10  "እኔግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። "


ናሆ 1:15  "እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል። "


ሐዋ 18:18 " ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጅግ ቀን ተቀምጦ ወንድሞቹንም ተሰናብቶ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ፤ ስእለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራ ኦስተላጨ ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ። "

Anchor 11

ሥርዓተ ሱባዔ

 

ሱባዔ ምንድን ነው? ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላው ያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ሽለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2.2፤ መዝ.118.164፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም «አንድ ሱባዔ ጾመ» ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም «ሁለት ሱባዔ ጾመ» እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ 

መቼ ተጀመረ?


ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ «መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡» ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ «ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ» ሲል ቃልኪዳን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምጦስ አንቀጽ አራት/፡፡


ሱባዔ ለምን?

የሰው ልጅ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፡፡ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡ «በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?» እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ. 7.22-25፡፡


ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ  /ሱባዔ/ ይገባል፡፡



እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ምንም የምንጠይቀው /የምንማፀነው/ ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኘው መልስ አይኖርም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡


ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- «ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው?» በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለሀገር ሰላም፣ ስለጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበትና ለሚማፀነውም መልስ የሚሰጥበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡

«አኃው ለተልእኮ በወጡበትአንዱን ድቀት አግኝቶት አድሯል፡፡ በነጋው «ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ» አለው፡፡ «እኔም እንጂ አግኝቶኛል ፤ይልቁን ስሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደቀደመው ኾነን እንኖራለን» ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡ ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ «ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢ ገብረእኁከል ፤ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ» የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡


ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባትቀን/ እንደጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ «ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ» የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡


የቅዱሳንን በረከት ለመሳተፍ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃልኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባዔ የቅዱሳኑን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ ቅዱሳን በሚጋደሉበት ቦታ «ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋ የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ»  /ኢሳ.56.6/ በማለት እግዚአብሔር ቃልኪዳን ስለገባላቸው ሱባዔ በመግባት በረከታቸውን መሳተፍ ይቻላል፡፡ በጾመነቢያት የነቢያትን በረከት ለመሳተፍ፣ በጾመሐዋርያት የሐዋርያትን በረከት ለመሳተፍ፣ በጾመ ፍልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፍ ሱባዔ መግባት የነበረና ወደፊትም የሚኖር የቤተክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡ ዛሬ ይህን ሥርዓት በመከተል የተለያዩ ቅዱሳንን በረከት ለመቀበል /ለመሳተፍ/ የቅዱሳን አፅም ካረፈበት ገዳም በጾም፣ በጸሎት፣ በጉልበትም ገዳማትን በማገልገል የቅዱሳንን በረከት ደጅ የሚጠኑ ምእመናንና መናንያን በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ 

ይኸውም በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ በምዕራፍ 2.9 እንደተመለከተው ነቢዩ ኤልሳዕ መምህሩን ኤልያስን በማገልገል የኤልያስ በረከት በእጥፉ በኤልሳዕ ላይ አድሮበታል፡፡ ይህን አብነት በማድረግ በየገዳማቱ በትሕርምት የሚኖር መናንያንን ያገለገሉበትን ገዳም አባት በረከት በእጥፍ እየተቀበሉ ለሌሎችም የሚያቀብሉ አባቶች በየገዳማቱ አሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ በስመ ገዳማዊ የምእመናንን ገንዘብ የሚዘርፉና የእውነተኛ መነኮሳትንና መናንያንን የተቀደሰ ሕይወት የሚያጐድፉ መኖራቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

የተሰወረ ምሥጢር እንዲገለጥልን በዘመነ ብሉይ እግዚአብሔር ለአንዳንድ ነገሥታት ራእይ በማሳየት ምሥጢርን ይሰውርባቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ የግብፁን ፈርዖን፣ የባቢሎኑን ናቡከደነፆርንና ብልጣሶርን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዘፍ.41.14-36፡፡ ዳን.4.9 ፤ዳን.5.4፡፡ እነዚህ ነገሥታት በግል ሕይወታቸውም ሆነ በመላው ሽክም ወደፊት ሊፈጸም የሚችል ራእይ ቢያዩም ቅሉ ራእዩን በትክክል ተረድተው «እንዲህ ይሆናል» የማለት ብቃት አልነበራቸውም፡፡ ስለዚህ በዘመናቸው ይኖር የነበሩትን ነቢያት ሱባዔ ገብተው የሕልማቸውን ትርጉም እንዲነግሩአቸው ይማፀኑ ነበር፡፡ ነቢያትም ሱባዔ በመግባት ነገሥታቱ ያዩትን የምሥጢረ ሥጋዌ ነገርና የመንግሥታቸውን አወዳዳቅ ገልጸው ይናገሩ ነበር፡፡ ዳን.5.28፡፡

እንዲሁም ቅዱሳን በየራሳቸው ያዩት ራእይ ምሥጢር ሲከደንባቸው የራእዩ ምሥጢርና ትርጉም እንዲገለጥላቸው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ዕዝራ የመጻሕፍትን ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ቢገባ የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ዳግም መልሶ ለመጻፍ ችሏል፡፡ መዝ.8.1፡፡


በዘመነ ሐዲስ በሰፊው የሚወሳው ቅዱሳን ሐዋርያትከ ነሐሴ 1-14 የገቡት ሱባዔ ነው፡፡ ይህ ሱባዔ ተሰውሮ የነበረውን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤ ተረድተው በረከቷን ለመሳተፍ አብቅቷቸዋል፡፡


«እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21 ቀን 50 ዓመተ ምሕረት ነው፡፡ ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴ ሰማኔ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ በታተኗቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችንንሥጋዋን ወስደው በገነት ከዕፀሕይወት ሥር አኑረውታል፡፡» /ተኣምረ ማርያም፤ ስንክሳር ነሐሴ 16 ቀን/፡፡ በዚህ ጊዜ እነርሱ ተደናግጠው ስለተበታተኑ የእመቤታችን የዕረፍቷ ያስጨንቃቸው ነበር፡፡ «ቅዱስ ዮሐንስ በተመስጦ እየሄደ ሥጋዋን ያጥን ነበር፡፡ ለሐዋርያት ይህን ይነግራቸዋል፡፡ ለዮሐንስ ተገልጣለ እኛ ሳትገለጥ ብለው በነሐሴ ሱባዔ ገቡ፡፡ ሁለተኛው ሱባዔ ሲፈጸም በ14ኛው ቀን መልአክ ሥጋዋን አምጥቶ ሰጥቶአቸዋል፤ ቀብረዋታል፡፡ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፡፡ /ተኣምረ ማርያም፤ ስንክሳር ነሐሴ 16 ቀን/፡፡


እንግዲህ ለቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችን የዕረፍትና የዕርገት ምሥጢር የተገለጠላቸው በሱባዔ ነው፡፡ ይህን መሠረት በማድረግ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን የዕርገቷን በረከት ለማግኘት ትጾማለች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህን የሱባዔ ወቅት ሕፃናትም ሳይቀሩ ይሳተፉታል፡፡


ሱባዔነቢያት
እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃልኪዳን መሠረት በማድረግ ቀደምት ነቢያት በተነሡበት ዘመን ቅደም ተከተል ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና ዳግም መምጣት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ሱባዔም ቆጥረዋል፡፡ ኢሳ.7.14፡፡ መዝ.49.3፡፡ ዘካ.13.6፤ ዘካ.14.1፡፡ የአንዱ ነቢይ ትንቢታዊ ንግግርና ሱባኤ በአነጋገርና በአቆጣጠር ከሌላኛው ነቢይ ጋር ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትንቢቱን ሲያናግር ምሳሌውን ሲያስመስል ጐዳናው ለየቅል በመሆኑ ነው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፡፡» እንዲል፡፡ ዕብ.1.1፡፡ የአቆጣጠር ስልታቸውና የሱባዔ መንገዳቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን አንድ ነው፡፡

ሱባዔ አዳም


አዳም ትንቢት በመናገርና ሱባዔ በመቁጠር የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ምክንያቱም በገነት ሰባት ዓመት ከአንድ ወር ከዐሥራ ሰባት ቀን በተድላና በደስታ ከኖረ በኋላ ሕግ በማፍረሱና የፈጣሪውን ቃል በመጣሱ ያለ ምንም ትካዜና ጉስቁልና ከሚኖርበት ዔደን ገነት ተባርሯል፡፡ ዘፍ.3.24፡፡ እርሱም ፈጣሪው እንዲታረቀው፣ በዐይነምሕረት እንዲጐበኘው፣ ቅዝቃዜው ሰውነት ከሚቆራርጥ ባሕር ውስጥ በመቆም ለሠላሳ አምስት ቀን /አምስት ሱባዔ/ ሱባዔ ገብቷል፡፡ በባሕርዩ የሰውን ልጅ እንግልት የማይወድ ቸሩ ፈጣሪ የአዳምን ፈጽሞ መጸጸት ተመልክቶ «በኀሙስ ዕለት ወበ መንፈቃ ለዕለት እትወለድ እም ወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብ ከወእቤዝ ወከበመስቀል የወበሞት የኸበ አምስት ቀን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ ተስፋውን ሰጠው፡፡ አዳም የተሰጠውን ተስፋ ይዞ በዓለመ ሥጋ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ አመት ከኖረ በኋላ መከራና ችግር ከበዛበት ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡



በወንጀል ተከሶ በወኅኒ የተፈረደበት ሰው ከእስር የሚፈታበትን ዕለት በማውጣት በማውረድ ወራቱንና ዓመታቱን እንደሚቆጥር፣ አዳምም በሞት ቢለይም በሲኦል የነፍስ ቅጣት ካለበት ሥፍራ ይኖር ስለነበር የተሰጠውን ተስፋ በማሰብ ሱባዔውን እየቆጠረ የተናገረውን የማያስቀር የማያደርገውን የማይናገር ጌታየ «እነሆ አድንኀለሁ» ብሎ የገባልኝ ዘመንተፈጸመ፤ ሰዓቱ አሁን ነው፤እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ቸር አምላክ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ፡- «ተንሥኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሡ፤ሰላም ለኩልክሙ፤ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት አዳምን ከነልጅልጆቹ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አዳምን በመከተል ልጆቹም አበውቅዱሳን ነቢያት ሱባዔ በመግባት የተስፋን ዘመን በመቁጠር በመልካም ግብር ተከትለውታል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ነቢያት በተለያየ ስልት ሱባዔ ቆጥረዋል፤ እኛም ሱባዔ ከቆጠሩ ነቢያት የተወሰኑትን በዚህ ጽሑፍ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

 

ሱባዔ ሔኖክ


ጻድቁ ሔኖክ፣ የያሬድ ልጅ ሲሆን፣ በትውልድ ከአዳም ሰባተኛ ነው፡፡ እርሱም በሕይወቱ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ቤት ንብረቱን በመተው በሱባዔና በትሕርምት እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡ ፍጹም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መልካም ግብር ተመስክሮለታል፡፡ «ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡» ዘፍ.5.22፡፡ ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የሱባዔውን ዋጋ ቅዱስ መንፈሱን በረድኤት ስለአሳደረበት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ በሰማይ ተሰውሮ ሳለ ስለቅዱሳን መላእክት፣ ስለ መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለፀሐይና ጨረቃ አመላለስ /ዑደት/ የሚተርክ በስሙ የተሰየመውን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘፍ.5 21-24፡፡ ይሁዳ ቁ.14፡፡ ሔኖክ 1.9፡፡


ሱባዔ ሔኖክ የሚባለው ነቢዩ ሔኖክ በመስፈርት የቆጠረው ሱባዔ ነው፡፡ መስፈርቱ  /ማባዣ ቁጥር/  35  ሲሆን 35'19 ሲበዛ በውጤቱ 685 ዓመትይሆናል፡፡ 685'12 ስናባዛው 7980 ይሆናል፡፡ ይኸውም ሐሳብ የሚያስረዳው ስለክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡ 

ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን የደረስንበት ዘመን 7497 ይሆናል፡፡ይህን ለማረጋገጥ በ5500 ዓመት ላይ 1997 ዓመትን መደመር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ከላይ ያስቀመጥነውን 7497 ዓመት ይሰጠናል፡፡ በነቢዩ ሔኖክ አቆጣጠር መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ በ7980 ይሆናል፡፡ ከላይ ሔኖክ የቀመረውን ቁጥር ይዘን ከ7980 ዓመት ላይ አሁን ያለንበትን ዘመን /1997/ ስንቀንስ 483 ዓመት እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በሔኖክ ሱባዔ መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን 483 ዓመት ይቀራል፡፡


ሱባዔ ዳዊት


ነቢዩ ዳዊት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ ንጉሥ ነበር፡፡ ዘመነ መንግሥቱ 1011-971 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደነበር ይታመናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ልበ አምላክ እንደ መሆኑ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ ይኽውም ቀመረ ዳዊት በመባል ይታወቃል፡፡ «እስመ ዐሠርቱም እትዓመት በቅድሜከ፤ ከመዕለት እንተ ትማልም ኃለፈት፤ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትላንት ቀን»፡፡ /መዝ.89.4/ የሚለውን መምህራን ሲቆጥሩት 1140 ዓመት ይሆናል፡፡ ይኸውም በጌታ ዘንድ 1140 ዓመት እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ ይህም ለዳዊት ሱባዔ መቁጠሪያ /መሥፈሪያ/ ሆኖ አገልግሏል፤ 1140’7= 7980 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በ7980 ዓመት ክርስቶስ ዳግም እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡


ሱባዔ ዳንኤል


ነቢዩ ዳንኤል ምድቡ ከዐበይት ነቢያት ነው፡፡ እስራኤል ወደ ባቢሎን ሲማረኩ ተማርኮ ወደ ባቢሎን ወርዷል፡፡ እርሱም ስለ ክርስቶስ መምጣት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔም ቆጥሯል፡፡ «ሰብአ ሰንበታ ተአድሞሙ ለሕዝብከ፤ ሰባ ሰንበት ወገኖችህን ቅጠራቸው፡፡» ይኸውም ክርስቶስ ከ490 ዓመት በኋላ ሰው መሆኑን የሚያመለክትትንቢትነው፡፡እንዲሁም «እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ትትሐነፅ መቅደስ ወእምዝ ትትመዘበር፤ እስከ ንጉሥ ክርስቶስ ድረስ መቅደስ ትታነፃለች በኋላም ትፈርሳለች» ሲል ተናግሯል፡፡


የአቆጣጠር ስልቱም በዓመት ሲሆን ይኸውም ሰባቱን ዓመት አንድ እያሉ መቁጠር ነው፡፡ ይኽውም ሱባዔ ሰንበት ይባላል፡፡ ዳንኤል ሱባዔ ከቆጠረበትና ትንቢት ከተናገረበት ጀምሮ ክርስቶስ እስከሚወለድ 490 ይሆናል፡፡ መስፈርቱ /ማባዣው/ ሰባት ስለሆነ 7’70 ስናባዛው 490 እናገኛለን፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሱባዔ ከቆጠረና ትንቢት ከተናገረ ከ490 ዓመት በኋላ የክርስቶስን መወለድ ያመለክታል፡፡ 

በአጠቃላይ ከላይ የተመለከት ናቸው ቅዱሳን ነቢያት አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሱባዔ ገብተው በትሕርምት በመኖራቸው ድንቅ የሆነውን የክርስቶስን ልደትና ዳግም ምጽአት ለመተንበይ ችለዋል፡፡ ሱባዔ መግባት የራቀን ለማቅረብ የረቀቀን ለማጉላት ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስገኝ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ 

የሱባዔ ዓይነቶች


የግል ሱባዔ /ዝግ ሱባዔ/


የግል ሱባዔ አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ በቤትና በአመቺ ቦታ የሚይዘው ማንም ሰው ሳያየው በግሉ የጸሎት በኣቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው እንዲሰማው በኅቡዕ የሚፈጽመው ሱባዔ ነው፡፡ ማቴ.6፡5-13፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ አንድ ሰው ሱባዔ ሲገባ ዘጋ ይባላል፡፡ ዝግ ሱባዔ የያዘ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ይዞ ወደ በኣቱ ከተከተተ በኋላ ሱባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከሰው አይገናኝም፡፡ መዝ. 101-6-7፡፡

 

የማኅበር ሱባዔ


የማኅበር ሱባዔ የሚባለው ካህናት፣ ምእመናን ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች በአንድ ሆነው በቤተክርስቲያንና አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው የሚገቡት ሱባዔ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ምእመናን ወደ እግዚአብሔር በመሄድ ይጸልዩ ነበር፡፡ 1ኛ ሳሙ.1፡9 ፤መዝ.121፡1 ፤ሉቃ.18፡10-14፡፡

 

በሐዲስ ኪዳንም የሐዋርያት ተከታዮች የኾኑ መነኮሳት፣ ካህናትና ምእመናን በገዳማት፣ በአድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ የጽዋ ማኅበርተኞች ስለማኅበራቸው ጥንካሬና ከማኅበርተኞቹ መካከል አንዱ ችግር ሲገጥመው የማኅበር ሱባኤ ይያዛል፡፡. 

የዐዋጅ ሱባዔ

 
የዐዋጅ ሱባዔ በአገር ላይ ድንገተኛ አደጋ፣ አባር ቸነፈርና ጦርነት ሲነደ እንዲሁም ለማኅበረ ምእመናን አስጊ የሆነ መቅሰፍት ሲከሰት፣ እግዚአብሔር መሽቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ ዓይነት ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ሱባዔ የነነዌ ሰዎችና በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ እስራኤላውያንተጠቃሾች ናቸው፡፡ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለሦስት ቀን ከመብል ከመጠጥ ተከልክለው በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔር መዓቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ አድርገዋል፡፡ ሌላው በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ አይሁድ በአስቴር ትእዛዝ የያዙት ሱባዔ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚያን ዘመን አርጤክስስ አይሁድ በያሉበት እንዲገደሉ በማዘዙ ከዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ለመዳን አይሁድ በዐዋጅ ሱባዔ ገብተዋል፡፡ አስቴር ገብታ ንጉሡን ስታናግረው ሌላው ሕዝብ በውጭ ዐዋጅ ዐውጀው ሱባዔ ገብተው ፈጣሪያቸውን ተማፅነዋል፡፡ አስቴር 4፡16 - 28፡፡ 

በአገራችንም ይህን የመሰለ የዐዋጅ ሱባዔ በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ተደርጓል፡፡ ፋሽስት ጣልያን አገራችንን በመውረር ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ድንበሯን አልፎ በመጣበት ወቅት ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ፡- «ጉልበትያለህ በጉልበትህ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ ርዳኝ» በማለት የዐዋጅ ሱባዔ መያዛቸው ይነገራል፡፡ በዚህም መሠረት በየገዳማቱም ሕላተ ይዟል፤ ንጉሡም ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው ዓለምን እጅግ ያስደነቀ ጥቁሮችን ለነጻነታቸው እንዲነሣሱ የሚያስችል ፋና ወጊ የሆነ ድል አግኝተው አገራችንን ለቅኝ ግዛት ያሰበውን ፋሽስት ጣልያንን ማሸነፋቸው በከፍተኛ ስሜት የምናስታውሰው ነው፡፡

 

ቅድመ ዝግጅት

 
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለ ምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተናያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ /፣ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት አስፈላጊ ነው፡፡ 

ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/

  
በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት አለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ 

ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሐ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ አባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሐ አባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡


ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው አንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተናመ ቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዐቅምንና ችሎታን አገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡


ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በአብዛኛው ሱባዔ የሚገባው አጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በአጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሐራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላነው፡፡ ምክንያቱም በአጽዋማት ወቅት ብዙ አባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከአባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡


እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ አይያዝም» የሚል አቋም ለመያዝ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ከአጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የሚያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ አያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና አድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡


ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/

 
በጸሎት ሰዓት ዓምድ ና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3 ፤መዝ.133፡2 ፤ ዮሐ.11፡41፡፡


በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀልኸ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡


በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙ ረዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ ፤ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሐራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡  ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡


በመጨረሻም ሱባዔ የገባሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡ 

ድኅረ ሱባዔ  /ከሱባዔ በኋላ/ 

ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባሰው ሁሉ ራእይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማፀን መጽናትይኖርብናል፡፡

Anchor 12

ጠበል

 

ጠበል ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ፍቺውም አፈር ማለት ሲሆን። ነገር ግን በቤተ ክርሲቲያናችን ጠበል ብለን የምንጠራው በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ሕሙማን የሚፈወሱበት ተአምራት የሚደረግበት ቅዱስ ውኃ ማለት ነው። ጠበል ማለት በግእዙ አፈር ማለት ከሆነ ሕሙማን የሚፈወሱበት ተአምራት የሚደረግበት ቅዱስ ውኃ ለምን ጠበል ተባለ? ቢሉ መልሱ በዮሃንስ ወንጌል ላይ የሚገኘው ቃል ነው፡፡


ዮሐ 9:6  "ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።" ይህ ተአምር የተደረገው ሥጋን የተዋሐደ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምራቁ ለውሶ ጭቃ ባደረገው መሬትና በሰሊሆም መጠመቂያ ከሚገኘው ቅዱስ ውኃ ድብልቅ በመሆኑ ሕሙማን የሚፈወሱበት ቅዱስ ውኃ ጠበል ተብሎ ተጠርቶአል::



ስለ ጸበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች

 

1ኛ.2ኛነገ 5:1-15 "የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃንዕ ማንም ለምጻም ሰው ነበረ።... ለእስራኤልም ንጉሥ። ይህች ደብዳቤ ወደ አንተ ስትደር ስባሪያዬን ንዕማንን ከለምጹ ትፈውሰው ዘንድ እንደሰደድሁልህ እወቅ የሚል ደብዳቤ ወሰደ። የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ወደ እኔ ይምጣ፥ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ። ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፥ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም ።ሂድ ፥በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ ሥጋህም ይፈወሳል፥። ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፥ እንዲህም አለ፦እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። ባሪያዎቹም ቀርበው። አባት ሆይ፥ ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር ይልቁንስ። ታጠብና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ! ብለው ተናገሩት። ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው እንደተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅጥልቅ አለ ሥጋውም እንደገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ።"


ዮሐ 5:2-5  "በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።"


ዮሐ 9:1-8  "ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ። ........ ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።" 

ሕዝ 36፥25  ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። 

ብዙዎችለምንየጸበሎችሥምበቅዱሳሥምይሰየማል? አዳኙም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ሳለ ስለ ምን የድንግል ማርያም ጸበል; የሚካኤል የገብርኤል ወዘት....ጠበልተባለ? መልሱ አጭር ነው :: ይኀውም በጠበሉ ቅዱሳኑ እንዲታሰቡ ነው::በ 
ኢሳያስ 56:4-6  "ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለመረጡ ቃል ኪዳኔንም ለጠበቁ ጃንደረቦች ከሴቶች ልጆችና ከወንዶች ልጆች ይልቅ የሚበል ጥበቤ ቴና በቅጥሬ መታሰቢያቸውን አደርጋለሁ:: የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለው" 

ምሳሌ 10:7 "የጻድቅ መታሰቢያው ለዘለአለም ነው"

 

በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በጠበሉ ቅዱሳኑ መጠራታቸው መታሰቢያቸው እንዲሆን ነው:: መታሰቢያም ብቻ ሳይሆን በረከትም አለው ብለን እናምናለን እንጂ ጠበሉን የፈጠረው መድኃኔአለም አምላካችን ኢየሱስክርስቶስ መሆኑና በጠበሉም አድሮ ሕሙማንን የሚፈውሰውና ተአምራትንም የሚያደርገው ሁሉን ቻይ የሆነው የአምላካችን የእግዚአብሔር ኃይል መሆን ጠፍቶን አይደለም:: በጠበል ታጥበን እንድንፈወስ የሆነው በሚታዩ በሚጨበጡ ቅዱሳት ምልክቶች የማይታየውን የማይጨበጠውን አጋንንትን ማባረር ሕሙማንን የመፈወስ ተአምራትን የማድረግ ረቂቅ ኃይሉን እንዲያስተላልፍባቸው ስለተፈቀደ ነው:: ለምሳሌ ያህል 

1.ዘዳ 14:15-17 የኤርትራን ባሕር የመክፈል ኃይሉን በሙሴ በትር


2.2ነገ 13:20 ሙት የማስነሳት ኃይሉን በዓጽመ ኤልሳዕ


3.ማር 6:14, ያዕ 5:14 ደዌያትን የመፈወስ ኃይሉን በቅዱስ ዘይት


4.ሐዋ 19:11 አጋንንትን የማባረር ኃይሉን ቅዱስ ጳውሎስ ለብሶት በነበረው ልብስ


እንዳስተላለፈ ሁሉ በዚህ ጠበል ተብሎ በተጠራው በቅዱሱ ውኃም እስከ አሁን ድረስ ወደፊትም ሕሙማን የመፈወስ ተአምራትን የማድረግ ረቂቅ ኃይሉን እያስተላለፈልን እየፈወሰን እንገኛለን:: ለዚህ ምሳሌ የአዲስ አበባ ኪዳነምህረት ተክለሃይማኖት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኡራኤልን.... የለበቃ ኢየሱስን ጠበል መጥቀስ በቂ ነው::

Anchor 13

ጾም

 

ጾም:- ለተወሰነ ጊዜ እህል ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት: ከሥጋ: ከቅቤ: ከወተት: ከእንቁላል: በአጠቃላይ ከእንሰሳት ውጤት መከልከል ነው:: ይህ ብቻ ጾምን ፍጹም ስለማያደርግ ሕዋሳት ሁሉ በየራሳቸው ክፉ ከመስራትመጠበቅ አለባቸው:: ይኽውም ዓይን ክፉ ከማየት ጆሮ ክፉ ከመስማትም ላስ ክፉ ከመናገር ይከልከሉ:: በተጨማሪም አእምሮን ጎድ ተውሰውን አስክረው የማይገባ ከሚያሠሩና ከሚያሳስቡ የአልኮል መጠጦች መጠበቅ እንዳለብን ማወቅ ይገባናል:: እንግዲ ከላይ የተገለጸውን የጾም ህግ ስንፈጽም ከጸሎት ተነጥሎ አይታይም: ጾምና ጸሎት በአንድነት ርኩሳን መናፍስትን ድል የምንነሳባቸው መሣሪያዎች ናቸው:: ጾማችንና ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የተራበ ልናበላ የታረዘን ልናለብስ ያስፈልጋል:: 

ስለጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ


ዘጸ 34:28 "ሙሴ በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃልኪዳን ቃሎች ጻፈ።"

 

መሳ 20:26  "የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደቤቴል መጡ፥ አለቀሱም፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፥ በዚያም ቀን እስከማታ ድረስ ጾሙ"


1ኛሳሙ 7:6 "ወደ ምጽጳም ተሰበሰቡ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፥ በዚያም ቀን ጾሙ"


1ኛሳሙ 31:13  "አጥንታቸውንም ወሰዱ በኢያቢስም ባለው በአጣጡ ዛፍ በታች ቀበሩት፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።"


2ኛሳሙ 1:12  "ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከማታም ድረስ ጾሙ።"


2ኛሳሙ 12:16 "ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ ዳዊትም ጾመ፥ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ።"


ዕዝ 8:21  "በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።"


ነህ 1:4  "ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌቀንም አዝን ነበር በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥"


ነህ 9:1 "በዚህም ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእስራኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብሰው ፥በላያቸውም ትቢያ ነስንሰው ተከማቹ።"


አስቴ 4:16  "ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ ብጠፋም እጠፋለሁ።"


መዝ 34:13  "እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።"


መዝ 68:10 "ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ለስድብም ሆነብኝ።"


መዝ 108:24  "ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።"


ኢሳ 58:3-6 "እኔ የመረጥሁት ጾምይህ ነውን?"


ኤር 36:9  "እንዲህም ሆነ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።"


ዳን 9:3  “ማቅ ለብሼ በአመድም ላይ ሆኜ ስጾም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ ወደ አምላክ አቀናሁ።"


ኢዩኤ 1:14  "ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።"


ኢዩኤ 2:12  "አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።"


ዮና 3:5 "የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"


ማቴ 4:2 "ኢየሱስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ጾመ"


ማቴ 6:16-18  "ስትጾሙም፥ እንደግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደጾመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል አንተ ግን ስትጾም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጾመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።"

ማቴ 17:20  "ኢየሱስም፦ ስለእምነታችሁ ማነስነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም። ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጾም በቀር አይወጣም አላቸው።" 

ማር 2:18  "ኢየሱስም አላቸው። ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጾሙ አይችሉም። ነገርግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ወራትምይጾማሉ።"


ማር 9:29 "ደቀመዛሙርቱ።እኛልናወጣውያልቻልንስለምንድርነው? ብለው ብቻውን ጠየቁት። ...ኢየሱስም ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው።"

 

ሉቃ 2;37  "እርስዋም ሰማኒያ አራት ዓመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።"


ሉቃ 18:12 "በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ"


ሐዋ 13:3 " በአንጾኪያም ባለችው ቤተክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ... እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጾሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጾሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።" 

ሐዋ 14:23 " በየቤተክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጾመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።" 

2ኛቆሮ 11:27 " በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጾም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ። የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።

Anchor 14

የጽዋ ማኅበር

 

ይህ ዓይነቱ ትውፊታዊ ሥራዓት አጀማመሩ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያ ተጠብቆ የኖረ ምእመናን በየተራ ምግብና መጠጥ አዘጋጅተው ከችግርኞች ጋር የሚሳተፉበት ሥርዓትነው:: በጌታ : በእመቤታችን : በቅዱሳን መላእክት : በጻድቃን : በሰማእታት ስም በመታሰቢያ ዕለታቸው ይፈጸማል::
የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖችን ሕይወት የሚያስታውስ ነው:: ይህ አብሮ መብላትና መጠጣት የአንድነት : የፍቅር ማዕድ አጋፔ (Agape) ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው:: በዚህም በረከት ይገኝበታል::  ምሳ 10:7 "የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል።"

ሐዋ 2:44 "ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።"

 

ዕብ 10:25 "በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስበርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።"


ሐዋ 4:32-37 "ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።"


ቆላ 2:5 "በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና ፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶ ስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።"

ቆላ 4፥16 ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ። ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።

Anchor 15
bottom of page