ሃራጥቃ ተሐድሶ

 

ተሐድሶ ማለት የቃሉ ጥሬ ትርጉም አዲስ ማድረግ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዐውድ ግን ተሐድሶ ማለት የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር በመቆጣጠር የቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ቀኖና፣ትውፊት እና ሥርዓት በመቀየር ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን የማንበር እንቅስቃሴ ነው፡፡

-ተሐድሶን በሃሳብ ጸንሶ በነቢብ ወልዶ በገቢር ያሳደገው መነኩሴ የነበረውና ቆቡን የጣለው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር ተሃድሶ፡፡ተሃድሶ በሚል ሽፋን  በይፋ መንቀሳቀስ የተጀመረው ማርቲንሉተር በካቶሊክ ቤተክርስትያን ላይ ባስነሳው ተቃውሞ በኃላም አሁን ላለው በቁጥር ከ 30ሺ በላይ ለተከፋፈለው ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት መመስረት ምክንያት ሆኖአል፡፡

በኦርቶዶክተዋህዶቤተክርስትያንላይየተሐድሶመናፍቃንዘመቻ

በ20ኛው መቶ ዓመት መጀመሪያ ላይ የግብጽ ቤተክርስቲያንን እናድናለን በሚልከው ስጣለ መለወጥ እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር::ሆኖም ግን የእነ ሊቀ ዲያቆን ሀቢብ ጊዮርጊስ መነሳትና በስንበት ት/ቤቶች በቴዎሎጂ ት/ቤቶች እና በመሳሰሉት ሁለ ገብ ዘርፎች ያደረገው ድካምና ውጤቱ ወደኃላ ላይም የእነ "ድሃው ማቴዎስ" መነሳትና በእነርሱ እንቅስቃሴ የአስቄጥስ ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት በአጠቃላይ ተዳክሞ ከነበረበት ሁኔታ እንደገና ማበቡ እንዲሁም የእነ አቡነ ሺኖዳ ትውልድ መነሳትና በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች እየተጠናከረ የመጣው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በተሃድሶ ሰበብ ሊካሄድ የነበረውን ወደፕሮቴስታንት የመለወጥ ስራ አክስሮል::

 

በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ላይም ተመሳሳይ የመውረር ዘመቻ አድርገዋል:: የፕሮቴስታን ተሃድሶ መሰሪ አካሄዳቸው የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሰምሮላቸው ቤተክርስቲያኒቱን ለሁለት መክፍል ችለዋል:: በዚህም ምክንያት እንድ የነበረችህ የህንድ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የታደሰች የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ተብላ ለሁለት ተከፍላ ቀርታለች::

ተሃድሶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ

ዛሬ ደግሞ ተሐድሶ በሚል ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ቡድን ፊቱን ወደጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፊቱን አዙራል:: ተሐድሶ የፕሮቴስታንቱን አለም አስተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን በማምጣት በቤተክርስቲያን ላይ ሥርነቀል አብዮት መምጣት አለበት የሚሉ አካላት ስብስብ ሲሆን፡፡ይህ አብዮት ዶግማዋን፣ቀኖናዋን፣ትውፊቷን፣ቅዳሴዋን፣ጸሎቷን፣ገዳማዊሕይወቷን፣ወዘተ የሚመለከት ነው ባይናቸው ነው፡፡ነባርዋን ቤተክርስቲያን አፍርሶ በለዘብተኛነት ወደ ፕሮቴስታንቱ አለም አስተምሮ መቀየር ግቡ ነው፡፡ተሐድሶ መነኮሳት አጠፉ ብሎ ምንኩስና ሕይወትን ለማጥፋት ይነሣል፤ጳጳሳት አጠፉ ብሎ ጵጵስናን ለማስቀረት ይጥራል፤በአንዳንድ ቀሳውስት ችግር ቅዳሴን ያስቀራል፤በተንዛዛ ድግስ ምክንያት ዝክር አያስፈልግም ይላል፤በአጠቃላይ የሥነምግባር ችግሮችን ከመሠረተ እምነት ጋር ይቀላቅላቸውና ቤተክርስቲያንን ከመሠረቷ ይንዳታል፡፡

የዚህ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ከሌላ እምነት የመጡ ሳይሆኑ ቤተክርስቲያኒቱ አሥተምራ ያሳደገቻቸው የእናትጡት ነካሽ የሆኑ መነኮሳት: የአብነት ተማሪ የነብሩ: ሰባኪያን እንዲሁ ምዘማሪያን በገንዘብ ከሚረዳቸው ከፕሮቴስታንቱ ክንፍ ጋር በጋራ በመሆን ቤተክርስትያኒቱን ሙሉ ለሙሉ ወደፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ለመለወጥ እንቅስቅሴ ላይ ናቸው:: በዚህም የዋሁን ምዕመን በልብሳችውና በአፋቸው ኦርቶዶክስ ነን በማለትና በቲፎዞነት በማሰለፍ በስብከቶቻቸውና በመዝሙሮቻቸው እንዲሁም በሚያሳትሙት መጻህፍት ኑፋቄአቸውን በመዝራት በስም ኦርቶዶክስ የሆነ ነገር ግን ኦርቶድክስን የማያውቅ፣ፕሮቴስታንት የሆነ፣ነገር ግን ተሐድሶ (ፕሮቴስታንት) መሆኑን እንኳን የማያውቅ ምዕመን ማፍራት፡፡

 

ስልቶቹም፡-

• የቤተክርስቲያኒቱን የትምህርት ጉባዔያት ይዘት መቀየር፣

• “ክርስቶስን አምላክነት ማስረሳት” ከሥላሴ ጋር ይለያያሉ ማለት፣

•“ኦርቶዶክስ እውነተኛ ቤተክርስትያን ነበረች፣ግን በየጊዛው የተጫኑባት ገለባዎች አሉ፣ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል፣የጥንቷን ቤተክርስቲያን መመለስ አለብን” ወዘተ እያለ ደጋግሞ መስበክ እንዲቀበለው ወይም ተቃውሞውን እንዲያለዝብ ማድረግ፣

•ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ስለ ነገረ ቅዱሳን፣ነገረ ማርያም፣ጾም፣ጸሎት፣ስግደት ወዘተ አስመልክቶ አለማስተማር፣ማስረሳት፣በዚህ ዙሪያ ማስተማር ለሕይወት የማይጠቅም ርባና የለሽ እንደሆነ ማስወራት

•ለመናፍቃን ምላሽ የሚሰጡ ሰባኪይንና ዘማሪያንን ማጣጣል

•ቤተ ክርስቲያንን ያረጀች ያፈጀች “አሮጊቷሣራ’’ አድርጎ በመቁጥር

•ቤተ ክርስቲያን ወንጌል አትሰብክም ብሎ ማስወራት

•ከቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውጪ ጉባኤአትን በየቡና ቤቶች ውስጥ በማዘጋጀት ህዝቡ ከቤተክርስቲያን እንዲርቅ ማድረግ

•በስብከቶቻቸው ውስጥ ካህናትን ዲያቆናትና ንጳጳሳቱን በመዝለፍና በመሳደብ ህዝቡ እንዲንቃቸው በነሱም እምነት እንዳይኖረው ማድረግ

•በስብከቶቻቸውና በመዝሙሮቻቸው ላይ ጥያቄ የሚያቀርብን ምዕመን ወንጌል ያልገባው በማለት መወረፍ

•መዝሙሮቻቸው ከመዝሙር የራቁ ለዘፈን ግን የቀረቡ መሆን በዚህም የዘፈን እርሾ ያለበት ወጣት ወደነሱ በማቅረብ ለአላማቸው ማስፈጸሚያ ማድረግ

 

አንቅስቃሴቸው በድብቅ እና በስውር ብቻ አይደለም በግልጥም በሚያሳትሙት መጽሔትና መጻህፍት ላይ በግልጽ አስቀምጠውታል ለምሳሌ ያህል፦•“ማርያምንም ሆነ ሌሎች ቅዱሳን አማልዱን ማለት ሙስና ሲሆን ሙስናን ለማጥፋት መጀመር ያለበት ይህን ትምህርት ከማጥፋት ነው፡፡” (ጮራ 30/1)

•“ዘማውያን የነበሩ ሰዎች በቅዱሳን አማላጅነት ምሕረትን አገኙ (ገድለ ጊዮርጊስን በመጥቀስ) የሚለ ታሪኮች ኤችአይቪኤዴስን ያስፋፋሉ፡፡”(ሰው የለም ወይ ? ገጽ 30)

•“መጽሐፈ ስንክሳር ፀረ ልማት ነው”(ሰውየለምወይ ? ገጽ 5)

ተሃድሶዎች ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል ሁኔታ ጥንታዊ ኦቶኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማትቀበላቸውን ነገር ግን የፕሮቴስታንቱ አለም የሚያስተምራቸውን አስተምሮዎች ይከተላሉ:: ለምሳሌ፦

•መዳን በእምነት ብቻ ነው

•ኢየሱስክርስቶስ አማላጅ ነው

•ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ አይደለችም

•ጾም; ቅዳሴ አያስፈልግም

•ቅዱሳን አያማልዱም

•ሃጥያትን ለንሰሃአባት መናዘዝን ይቃወማሉ

•ስርአተ ቤተ ክርስትያን አያስፈልግም

•ሁሉም ካህን ነው

•ምንኩስናን ማጣጣል

•ትውፊትን መቃወም

•አጽዋማት ይቀነሱ

•የዘፈን መሳሪያዎችን ለመዝሙር እንጠቀም

•አለባበስን በተመለከተ

•አዋልድ መጻህፍትን መቃወም እና ሌሎች በዛያሉ ከኦርቶዶክስ አስተምሮ የሚለዩ ትምህርቶችን ይከተላሉ::

 

ከእኛ ምን ይጠበቃል

1.የተሐድሶን ምንነትና ሊያስከትል የሚችለውን አደጋና ጥፋት በትክክል መረዳት፣

2 ከቲፎዞነት መውጣት

በቤተክርስቲያን ጉዳይ ጥብቅና ልንቆም የሚገባው ወገንተኛም ልሆን የሚገባው ለቤተክርስቲያን ነው፡፡ይህም ማለት ለዶግማዋ፣ለሥርዓቷ እና ለትውፊቷ ማለት ነው፡፡ስለሰዎች የምንነጋገረው ከእነዚህ ነገሮች አንፃር መሆን አለበት፡፡እኛ ሰዎችን በቤተ ክርስቲያን በኩል አገኘናቸው እንጂ ቤተክርስቲያንን በሰዎች በኩል አላገኘናትም፡፡ቤተክርስቲያን ፓትርያርኮችን፣ጳጳሳትን፣ቀሳውስትን፣ዲያቆናትን፣ሊቃውንትን፣ሰባክያንን፣መዘምራንን አፈራች እንጂ እነርሱ አላስገኟትም፡፡በመሆኑም የሰዎች እና የቡድኖች ቲፎዞ በመሆ ንዶግማዋን፣ሥርዓቷን እና ትውፊቷን ከማፍረስ መቆጠብ አለብን፡፡

ሰውን መውደድ፣ማድነቅ እና ማክበር መልካም እና ክርስቲያናዊ ምግባርም ነው፡፡ያ ማለት ግን ክፉ ሥራውን መውደድ፣ማድነቅ እና ማክበር ማለት አይደለም፡፡ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ በጻፈው ደብዳቤ «ንስጥሮስ ሆይ አንተን እወድድሃለሁ፤ኑፋቄህን ግን እጠላለሁ» ያለውን መርሳት የለብንም፡፡እገሌ የሀገሬ ልጅ ነው፣ውለታው አለብኝ፤ድምጹ ደስ ይለኛል፣አሰባበኩ ያምራል፣አብሮ አደጌነው ወዘተ እያልን ጥፋታቸውን በዝምታ ያለፍናቸው ሰዎች ተቀምጠን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ እንዳንችል አድርገውናል፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ወልደ ነዌ በአንፃረ ኢያሪኮ በተገለጠ ጊዜ ኢያሱ «ከኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን?» ሲል ጠይቆት  ነበር፡፡ቅዱስሚካኤል ግን የወገንተኛነትን ጥያቄ አልመለሰም፡፡ «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ» ነበር ያለው፡፡ «የእግዚአብሔር ከሆነው ጋር ነኝ» ማለቱ ነበር፡፡በመሆኑም መመዘኛችን ከእግዚአብሔር ጋር የሆነ ማንነው? የሚለው እንጂ የኔወገን ማንነው? የሚለው መሆን የለበትም፡፡

በሌላም በኩል እኛ የክርስቶስ ነን ማለትን መልመድ አለብን፡፡የአቡነ እገሌ፣የቄስ እገሌ፣የአባ እገሌ፣የባሕታዊ እገሌ፣የሰባኪ እገሌ፣የዘማሪ እገሌ፣የማኅበረ እገሌ፣አይደለንም፡፡የጎንደር፣የጎጃም፣የትግሬ፣የወሎ፣የሸዋ፣የወለጋ፣የሲዳሞ፣የከፋ፣የሐረር፣የባሌ፣የጉሙዝ፣የአፋርአይደለንም፡፡እኛ የክርስቶስ ነን፡፡የክርስቶስ ከሆኑት ጋርም አብረን እንቆማለን፡፡የሚያገናኘን ሃይማኖት እንጂ ዘር፣ፖለቲካ፣ወንዝ፣ተራራ፣አብሮአደግነት፣ጉርብትና፣አይደለም ብለን ለራሳችን ማሳመን እና መቁረጥ አለብን፡፡

ቲፎዞነት ጭፍን ድጋፍ እና ተቃውሞን ያመጣል፡፡ነገሮችን በሰከነ መንፈስ፣በሕግ እና በሥርዓት አንፃር፣ከታሪክ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት አንፃር፣ከተጠየቅ እና ከማስረጃ አንፃር ከመገምገምና አቋም ከመያዝ ይልቅ እነማን አሉበት? እነማን ተናገሩ? ወገኖቼ ናቸው አይደሉም? በሚል መመዘኛ ብቻ ወደ መቃወምና መደገፍ ይወስደናል፡፡ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ የመከረውን ትቶ አኪላስ አርዮስን ለመሾም የበቃውአብረው የተማሩ የትምህርት ቤት ጓደኞች በመሆናቸው ከሕጉ ዝምድናው በልጦበት ነበር፡፡ነገር ግን አኪላስም በመንበሩ አልሰነበተም፣ለቤተክርስቲያንም ነቀርሳ አተረፈላት፡፡ቲፎዞነትም ውጤቱ ይኼው ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የዳዊትን እና የዮናታንን ወዳጅነት እናስብ፡፡ዮናታን የንጉሡ የሳኦል ልጅ ነው፡፡አባቱ ቢሞት ወራሽ ነው፡፡ዳዊት ደግሞ መንበሩን ይወርሳል የተባለ ሰው ነው፡፡ዮናታን የአባቱ ቲፎዞ ሆኖ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ከመጋጨት ይልቅ እግዚአብሔር አብሮት ከሆነው ከዳዊት ጋር መሆንን መረጠ፡፡በሥጋ፣በዝምድና እና በጥቅም ሳኦል ይሻለው ነበር፡፡ዳዊት የአባቱን መንበር እንደሚወስድ እያወቀ እንኳን ሥልጣን ሳያጓጓው ለእውነት መቆምን መረጠ፡፡

ግሪኮች ዲዮስቆሮስ ያለሕግ ሲባረር እና ሃይማኖት በኬልቄዶን ስትፈርስ የሮም ቲፎዞ ሆነው አጨበጨቡ፡፡ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ ግን እነርሱ ራሳቸው ከሮም ተለዩ፡፡መጀመርያውኑ ከቲፎዞነት ይልቅ ለሃይማኖት ቢያደሉ ኖሮ ይህ ሁሉ ባልደረሰ ነበር፡፡

3.ጉዳያችን ከግለሰቦች ወይም ከመሳሰሉት ነገሮች ለይቶ ከመሠረታቸውና ከጽንሰ ሃሳባቸው ማየትና መገንዘብ፣

4.ይህን የተሐድሶ አደጋ ለሌሎችም በትክክለኛ ሁኔታ ማሳወቅና ማስገንዘብ፣

5.በቅርብና በሩቅ የሚከሠቱ የተለያዩ ነገሮችን በንቃትና በተጠንቀቅ መከታተልና መረጃ መለዋወጥ፣ቤተክርስቲያኒቱን ከበለጠ አደጋ መታደግ፣

6.ተሐድሶዎች ቤተክርስቲያናችንን እንዲይ ከፍሏት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና እንዲህ እንዲሆን ምን ምዓይነት ዕድል አለ መስጠት፣

7.ሰንበት ት/ቤቶችንና ዓውደ ምሕረቶችን ማጠናከርና ከስብከተ ወንጌል ጋር በመተባበር መቆጣጠር፣ቀሳጮች ገብተው ጉዳት እንዲያደርሱ መከታተል፣

8.የጮኸ ሁላ የቤተክርስቲያንን ትምህርት አያስተምርምና የሚጋበዙ መምህራንና ዘማርያን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና መከታተል፣

9.የመረጃ አያያዝ መንገድን ማሻሻልና በተገቢው መልክ መጠቀም፣በአጠቃላይ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኒቱ አባል በዚህ ወሳኝ የቤተክርስቲያን የፈተና ወቅት ላይ መሆኑን ተገንዝቦ ከአምሊካዊና የትውልድ ወቀሳ ለመዳን ሁኔታው የሚጠይቀውን ነገር ሁለ ለማድረግ በመንፈስና በጸሎት ራስን ማዘጋጀትና ላልች እንዲሠሩ መጠበቅ ሳይሆን የራስን ድርሻ በመወጣት ላይ የተመሠረተና የተቀናጀ፣ውጤት የሚያመጣ ሥራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆን::

አምላከቅዱሳn ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ::

 

ሃይማኖትይታደሳል?

ዶግማየሚለውቃል “ዶኪን” ከሚልየግሪክግሥ (አንቀጽ) የተገኘነው፡፡በጥንቱግሪክኛቋንቋ “ዶኪንሚ” የሚለውአገላለጽወደአማርኛአገላለጽሲቀየር ወስኛለሁ፤እርግጠኛነኝ፤ጽኑዕእምነቴነው ማለትነው፡፡ 
ስለዚህዶግማማለትእርግጠኛየሆነነገር፣የተወሰነነገር፣የታመነነገርማለትነው፡፡ይህንእውነተኛ (የታመነ) ነገር፣የተረጋገጠነገር፣የተወሰነነገርደግሞበቤተክርስቲያናችንአተረጓጐምዶግማሲባልየሃይማኖትአባቶችየማይቀየር፣የማይሻሻል፣የማይለወጥ፣የማያረጅብለውይፈቱታል፡፡አዎለዚህምነውቅድስትቤተክርስቲያንሃይማኖትአይሻሻልም፤አይታደስምብላየምታስተምረው፡፡ 

ተሐድሶበኢኮኖሚ፣በፖለቲካ፣በአስተዳደር፣በልማት፣… ወዘተያስፈልጋል፤ሃይማኖትግንአይታደስም፡፡ስለሆነም “ሰማይናምድርያልፋሉ፤ቃሌግንአያልፍም” የሚለውንማስተዋልይገባል /ማቴ.24፡35/፡፡ማለትምራሱጌታየተናገረውንየቃሉንጽኑነት፣ተአማኒነት፣እርግጠኝነት፣ልክነትበትክክልያረጋግጣል፡፡ዶግማየሚለውቃሉየተመረጠውምከላይእንደተገለጠውእርግጠኛነትንየሚያመለክትቃልሆኖበመገኘቱነው፡፡… በኦሬንታልአብያተክርስቲያናትአተረጓጐምመሠረትዶግማየምንለው፡- Øሃይማኖታዊየሆነእውነታ፤Øበመለኰትመገለጥየተመሠረተ (የተገኘ) እናØቤተክርስቲያንየምታስተምረውትምህርትነው፡፡… አንድሰውመናፍቅሆነየሚባለውዶግማንከእምነቱሕግናሥርዓትውጭእናሻሻል፣እናድስበሚልአመለካከትከትክክለኛውአባባልናአነጋገርእንዲሁምአስተሳሰብወጥቶሲገኝብቻነው፡፡አዛብቶሳይተረጕምእንዲያውምወደሃይማኖትፈጽሞሳይገባበውጭሆኖየሚለፈልፍሰውግንሃይማኖትአልባ፣ከሐዲወይምአስተያየትሰጪነው፡፡እየተደረገናእየተባለካለውሁሉበሃይማኖትጸንተንእግዚአብሔርበምሕረቱበቸርነቱስለጐበኘንተስፋአንቆርጥም፡፡ስውርናአሳፋሪየሆነውንነገርአስወግደንበተንኰልምአንሠራም፤የእግዚአብሔርንምቃልከውሸትጋርአንቀይጥም፤ይልቅስእውነቱንበይፋእናሳያለን፡፡

ራሳችንንምበሰውኅሊናግልጥእያደረግንበእግዚአብሔርፊትእንኖራለን፡፡ያበሠርነውየምሥራችቃልምናልባትየተሠወረቢሆንምየተሠወረባቸውለሚጠፉትነው፡፡እነርሱምየማያምኑበትምክንያትለጊዜውየዚህዓለምአምላክ/ገዢየሆነውሰይጣንልቡናቸውንስላሳወረውነው፡፡በየአቅጣጫውመከራይደርስብናል፤ግንአንሸነፍም፡፡አንዳንድጊዜግራይገባናል፤ግንተስፋአንቆርጥም፡፡ጠላቶችያሳድዱናል፤ነገርግንወዳጆችአጥተንአናውቅም፡፡ተመተንእንወድቃለን፤ግንአንሞትም፡፡የጌታችንየመድኃኒታችንየኢየሱስክርስቶስሕይወትበእኛሰውነትእንዲገለጥዘወትርየመድኃኒታችንየኢየሱስንሞትበሰውነታችንተሸክመንእንዞራለን፡፡የእርሱሕይወትበሚሞተውሰውነታችንእንዲገለጥ “አመንሁ፤ስለዚህምተናገርሁ” ተብሎእንደተጻፈእኛምያውአንዱየእምነትመንፈስስላለንእናምናለን፤ስለዚህምእንናገራለን፤እንጽፋለንም /2ቆሮ.4፡1/፡፡

 

ሃራጥቃተሐድሶዎችየተሟላመጽሐፍቅዱስንአይቀበሉም

·        ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ)፦ከመጽሐፍቅዱስክፍሎችየሚፈልጓቸውንብቻበመውሰድሌሎችንትተዋቸዋል።በመሆኑምእነርሱበሚቀበሏቸውእናቤተ-ክርስቲያናችንበምትቀበላቸውመጻሕፍትቁጥርመካክልልዩነትአለ። 
1.የፕሮቴስታንቲዝምመስራችማርቲንሉተርለእርሱትምህርትየማይመቹየመሰሉትንመጻሕፍትእያወጣይጥልነበር።ለምሳሌ፦የያዕቆብመልእክትስለምግባርአስፈላጊነትሰለሚያስተምርናይህምማርቲንሉተርስለጸጋእናእምነትበቻይሰብከውከነበረውትምህርቱጋርአልሄድስላለውመልእክቱንከመጽሐፍቅዱስውስጥአውጥቶትነበር።እንዲያውም “Epistle of straw ገለባመልእክት” ብሎእስከመጥራትደርሶነበር። 

2.አንዳንድወገኖችከ66ቱመጻሕፍትውጭያሉትንመጻሕፍት “አፖክሪፓ” ብለውይጠሯቸዋል።ይህግንየተሳሳተስያሜነው። “አፖክሪፓ” በጥንትዘመንምሥጢራዊለሆኑትየጥንቆላመጻሕፍትየሚሰጥስምነውና።እኛግን፥የብሉይኪዳንመጻሕፍቱን፦ “ሁለተኛየቀኖናመጻሕፍት - ዲዮካትሮኒካል” እንላቸዋለን። 

3.የብሉይኪዳንመጻሕፍትሁለትዓይነትየቀኖናክፍሎችአሏቸው።እነርሱም፦የመጀመርያ-ፕሮቶካኖኒካል፣እናሁለተኛ- ዲዮካትሮኒካልይባላሉ። 
የመጀመርያ /ፕሮቶካኖኒካል/፦ 
እነዚህበካህኑበዕዝራየተሰባሰቡናመጀመርያበቀኖናየተመዘገቡናቸው። /1ኛመቃ 2፥10/ ነህምያምየነገሥታትንመጻሕፍትየያዘቤተ-መጻሕፍትአቋቁሞነበር።እነዚህመጻሕፍትበሦስትየተከፈሉሲሆኑ፥ቶራሕ፣ነበኢምእናከተቢምተብለውጠራሉ።ዕዝራእናነህምያሁለተኛዎቹንመጻሕፍትበተመለከተያነሱትነገርየለም።ምክንያቱምበዚያዘመንአልተሰበሰቡምና።የተሰበሰቡትከእነርሱበኋላበመሆኑ፤ “ዲዮካትሮኒካል - ሁለተኛ” ተበለዋል። 
ቶራሕ፦ 
አምድቱየሙሴመጻሕፍትንየያዘሲሆን፤በእኛሊቃውንት፥ “አምስቱበሔረኦሪት” ተበሎይጠራል። 
ነበኢም፦ 
የነቢያትመጻሕፍትየተካተቱበትክፍልሲሆን፤እነርሱም፦ “ቀደምትነቢያት” እና “ደኃርትነቢያት” ተብለውለሁለትይከፈላሉ። “ቀደምትነቢያት” የሚሏቸው፦ኢያሱ፣ሳሙኤል፣እናነገሥትናቸው። “ደኃርትነቢያት” የሚሏቸውደግሞኤርምስ፣ሕዝቅኤል፣ኢሳስእናአስራሁለቱደቂቃንነቢያትንነው።በሐዋርያትሥራ 13፥15 ያነበቧቸውእነዚህንመጻሕፍትነው። 
ከተቢም፦ 
የታሪክመጻሕፍትማለታቸውነው።እነዚህምበሁለትየሚከፈሉሲሆንታላላቅእና “ታናናሽየታሪክመጻሕፍትይባላሉ። “ታላላቅየታሪክመጻሕፍት” ማለትም፦መዝሙራት፣ኢዮብ፣ምሳሌ፤ “ታናናሽየታሪክመጻሕፍት” ማለትም፥መክብብ፣መኃልየመኃልየ፣ሰቆቃውኤርምያስናቸው።ከእነዚህምቀጥሎመጽሐፈዳንኤል፣ዕዝራ፣ነህምያእናዜናመዋዕልናካዕልይከተላሉ።እነዚህሁሉተጠቃለውየሙሴሕግ፣ነቢያትእናመዝሙራትእየተባሉይጠራሉ። 

ሁለተኛ /ዲዮካትሮኒካል/፦ 

1.የሂጶጉባኤበ393 ዓ/ምዲዮካትሮኒካልመጻሕፍትንእውነተኝነትናሊጠቀሱየሚችሉመሆኑንአረጋግጧል። 

2.በ397 ዓ/ምየተደረገውየካርታጎ /ቅርጣግና/ ጉባኤምተመሳሳይውሳኔሰጥቷል። 

3.በሦስተኛውመ/ክ/ዘየነበሩትእነቀሌምንጦስዘሮም፣እነዲዮናድዮስዘእስክንድርእንዲሁምሲፕሪያን፤ምስክርነታቸውንሰጥተዋል። 

4.በአራተኛውመ/ክ/ዘአበውእነባስልዮስ፣ጎርጎርዮስዘኑሲስ፣ዮሐንስአፍወቅር፤እየጠቀሱአስተምረውባቸዋል። 

5.እነዚህመጻሕፍትየሐዋርያትቀኖናበተሰኘውየሐዋርያትድንጋጌውስጥበዝርዝርተገልጠዋል። 

6.ጥንታውያንየሆኑትአብያተክርሰቲያናት፥ማለትም፦የካቶሊክ፣የግሪክኦርቶዶክስ፣እንዲሁምኦርየንታልአብያተክርሰቲያናትሁሉይቀበሏቸዋል።የኢትዮጵያቤተ-ክርስቲያንከጥንትጀምሮስትቀበላቸውየኖረችሲሆን፤በሲኖዶስደረጃበ1988 ዓ/ምውሳኔሰጥታለች። 

7.በበጥሊሞስሁለተኛዘመንበ282 ቅ.ል.ክበእስክንድርያብሉይኪዳንንወደግሪክየተረጎሙትሰባሊቃናትዲዮካትሮኒካልመጻሕፍትንአብረውተርጉመዋል።የሰባሊቃናትትርጉምሦስትቅጅዎችየሆኑት፦የሲና፣የእስክንድርያእናየቫቲካንቅጅዎችንብንመለከትእነዚህንመጻሕፍትአካትተውእናገኛለን። 

8.
በዮሐ 10፥22 የምናገኘውየመቅደስመታደስበዓልበሌሎችየብሉይኪዳንመጻሕፍትውስጥአናገኘውም፤በመጽሐፈመቃብያንወንድሞቹከእስራኤልሕዝብጋርየወሰኑትበየዓመቱመከበርያለበት፣የመታደስበዓልከመጽሐፈመቃብያንበቀርሌሎችየብሉያትመጻሕፍትላይአልተጠቀሰም።ነገርግንዮሐንስበወንጌሉ 10፥22 ላይይህንንበዓልጠቅሶትመገኘቱናሌሎችማስረጃዎችየመጻሕፍቱንቅድሰናያረጋግጡልናል።የሚገኘውምበ1ኛመቃ 4፥59 ላይነው። 

9.
በሉቃ 14፥13 “ነገርግንግብዣባደረግህጊዜድሆችንናጕንድሾችንአንካሶችንምዕውሮችንምጥራ፤የሚመልሱትብድራትየላቸውምናብፁዕትሆናለህ” የሚለውከጦቢት 4፥7፣ 10፥17 የተገኘነው። 

10.
በ1ኛተሰ 4፥3 “ይህየእግዚአብሔርፈቃድእርሱምመቀደሳችሁነውናከዝሙትእንድትርቁ” የሚለውቃልከጦቢት 4፥13 የተገኘነው። 

11.
በ1ኛቆሮ 10፥9 “ከእነርሱምአንዳንዶቹጌታንእንደተፈታተኑትበእባቦቹምእንደጠፉጌታንአንፈታተን” የሚለውቃልከዮዲት 8፥24 የተገኘቃልነው። 

12.
በ1ኛቆሮ 15፥32 “ሙታንስየማይነሡከሆነ፥ምንይጠቅመኛል? ነገእንሞታለንናእንብላናእንጠጣ” የሚለውከጥበብ 2፥6 የተገኘቃልነው። 

13.
በዮሐ 7፥7 “ዓለምእናንተንሊጠላአይቻለውም፤እኔግንሥራውክፉመሆኑንእመሰክርበታለሁናእኔንይጠላኛል።” የሚለውየጌታችንትምህርትበጥበብ 2፥13 ይገኛል። 

14.
በሉቃ 16፥9 “እኔምእላችኋለሁ፥የዓመፃገንዘብሲያልቅበዘላለምቤቶችእንዲቀበሏችሁበእርሱወዳጆችንለራሳችሁአድርጉ” የሚለውትምህርትበሲራክ 14፥13 ይገኛል። 

15.
በ1ኛጴጥ 1፥24 “ሥጋሁሉእንደሣር፣ክብሩምሁሉእንደሣርአበባነውና፤ሣሩይጠወልጋልአበባውምይረግፋል” የሚለውቃልከሲራክ 14፥18 የተገኘነው። 

16.
በሮሜ 13፥1 ፤ 1ኛጴጥ 2፥13 የተገለጠው “ከእግዚአብሔርካልተገኘበቀርሥልጣንየለምና፤ያሉትምባለሥልጣኖችበእግዚአብሔርየተሾሙናቸው” የሚለውቃልከሲራክ 17፥14 የተወሰደነው። 

17.
በይሁዳ 14 የተጠቀሰው “ከአዳምጀምሮሰባተኛየሆነሄኖክ።እነሆ፥ጌታበሁሉላይእንዲፈርድ፥በኃጢአተኝነትምስላደረጉትስለኃጢአተኛሥራቸውሁሉዓመፀኞችምኃጢአተኞችበእርሱላይስለተናገሩስለጭከናነገርሁሉኃጢአተኞችንሁሉእንዲወቅስከአእላፋትቅዱሳኑጋርመጥቶአልብሎለእነዚህደግሞትንቢትተናገረ።” በማለትየሄኖክትንቢትጠቅሶጽፏል።በመጽሐፈሄኖክ 1፥9 ላይይገኛል። 

18.ወንጌላዊውማቴዎስምበምዕራፍ 27፥9 ላይ፤የመጽሐፈተረፈኤርምያስንጠቅሶ “በዚያንጊዜበነቢዩበኤርምያስየተባለው፥ከእስራኤልልጆችምአንዳንዶቹየገመቱትን፣የተገመተውንዋጋሠላሳብርያዙ፥ጌታምእንዳዘዘኝስለሸክላሠሪመሬትሰጡት፤የሚልተፈጸመ።” በማለትጽፏል።ማቴዎስነቢዩኤርምያስንጠቅሶየፃፈውበ66ቱየትንቢተኤርምያስመጽሐፍውስጥየለም።ነገርግንመናፍቃን (ተሐድሶ) አንቀበልምከሚሉትመጽሐፍከተረፈኤርምያስ 7፥5 ይገኛል። 

19.አዳምናሔዋን፥አቤልእናቃየንቃየልንወለዱ።ቃየልአቤልንገድሎሸሸ።ከዚያምሚስቱንዐወቀ፣ፀነሰችም።ይህቺየቃየልሚስትከየትመጣች? እንደኦሪትዘፍጥረትከሆነ፦በምዕ 24 ላይ፥በዓለምላይያሉትሰዎችአራትብቻናቸው። (አዳም፣ሔዋን፣አቤል፤ቃየል) ነበሩ።የዚህንመልስየምናገኘውበኩፋሌ 5፥8-17 ነው። 

20.በዕለተሆሳህና፥ዘንባባይዘውጌታችንንየኢየሩሳሌምሰዎችሲያመሰግኑትውለዋል።የዚህትውፊት፥ታሪካዊአመጣጥየሚገኘው፤በዮዲት 15፥12 እናበኩፋሌ 13፥21 ላይነው። 

21.
በትንቢተኤርምያስ 39፥15 ስለኢትዮጵያዊውአቤሜሌክየተነገረውትንቢፍጻሜውንየምናውቀው፤በተረፈኤርምያስከምዕራፍስምንትጀምሮያለውንስናነብነው። 

በተጨማሪም፥ተከራካሪዎችካስወጧቸውእናከማይቀበሏቸውየብሉያትመጻሕፍትጋርተመሳሳይነትያላቸውየሐዲስኪዳንጥቅሶችአሉ። 
ለምሳሌ፦ጦቢት 4፥7 ከማቴ 6፥19-20 ጋር 
ጦቢት 4፥16 ከማቴ 7፥12 ጋር 
ዮዲት 8፥12 ከማቴ 4፥7 ጋርብናነፃፅራቸውተመሳሳይነታቸውበቂማሳረጃነው። 

በመሠረቱየብሉይኪዳንመጻሕፍትሁሉተቀባይነትእንዲኖራቸውለማድረግየግድበሐዲስኪዳንመጠቀስአለባቸውየሚልየሃይማኖትድንጋጌየለም።እንዲህቢሆንኖሮ፤ለምሳሌ፦ከመጽሐፈአስቴር፣ከመጽሐፈመክብብ፣ከመኃልየመኃልየዘሰለሞን፤በሐዲስኪዳንየተጠቀሰየለምናተቀባይነትየሌላቸውመጻሕፍትናቸውበተባለነበር። 
ስለዚህከአጠቃላይመናፍቃን (ተሐድሶ) መጻሕፍትንበጥንቃቄካለማንበብየተነሣበሐዲስኪዳንአልተጠቀሱምለሚሉትእነዚያካልተቀበሏቸውመጻሕፍትበሐዲስኪዳንእንደተጠቀሱተመልክተናል።እነዚህንመጻሕፍትየተቀበልናቸውበሐዲስኪዳንስለተጠቀሱምስላልተጠቀሱምአይደለም፤ነገርግንእውነተኝነታቸውንበማረጋገጥነው።

 

ሃራጥቃውያንትውፊትንይቃወማሉ

 

ቤተክርስቲያንንእናድሳለንየሚሉከሚቃወሞቸውመካከልትውፊትአንዱነው።እኛግንመጽሐፍቅዱስንመሠረትበማድረግትውፊትቤተክርስትቲያንንእንቀበላለን። 
ትውፊትማለትቅብብልማለትነው። 
ይሁዳ 1:3 "ለቅዱሳንአንድጊዜፈጽሞስለተሰጠሃይማኖትእጽፍላችሁዘንድግድሆነብኝ።" በሚለውየሐዋርያውየይሁዳትምህርትላይ "የተሰጠ" ሲልሰጭናተቀባይወይምውርርስትውፊትመኖሩንያመለክታል።ሐዋርያውቅዱስጳውሎስም 
1ኛቆሮ 11:23 "ለእናንተደግሞአሳልፌየሰጠሁትንእኔከጌታተቀብያለሁና" ይላል። 
አሳልፌየሰጠሁትእናከጌታተቀብያለሁየሚሉትአገላለጦችሰጭእናተቀባይንወይንምትውፊትንየሚያመለክቱናቸው። 

የቤተክርስቲያንትውፊትመጽሃፍቅዱስየቤተክርስቲያንንጸሎትየትምህርተሃይማኖትድንጋጌዎችንየቤተክርስቲያንንጉባኤያትየአበውትምህርትንእናጽሁፍየቅዱሳንንሕይወትእንዲሁምቀኖናዋንያካትታል። 
የቤተክርስቲያንንትውፊት "ሐዋርያዊትውፊት" ወይንምደግሞ "የተቀደሰትውፊት" እንለዋለን።ሐዋርያውቅዱስጳውሎስምይህንንትውፊትእንድንጠብቀውሲያስተምረን 
2ኛተሰ 2:15 "እንግዲያስ፥ወንድሞችሆይ፥ጸንታችሁቁሙ፥በቃላችንምቢሆንወይምበመልእክታችንየተማራችሁትንወግያዙ።" 
እንዲሁምበተጨማሪ 
2ኛተሰ 3:6 "ወንድሞችሆይ፥ከእኛእንደተቀበለውወግሳይሆንያለሥርዓትከሚሄድወንድምሁሉትለዩዘንድበጌታችንበኢየሱስክርስቶስስምእናዛችኋለን።" 

የሐዋርያትትውፊትበቅብብልከዘመናችንደርሷል።ይህንንትውፊትየሚጠብቅትውልድምይመሰገናልእንጂአይነቀፍም 
1ኛቆሮ 11:2 "ወንድሞችሆይ፥በሁሉስለምታስቡኝናአሳልፌእንደሰጠኋችሁወግንፈጽማችሁስለያዛችሁአመሰግናችኋለሁ።" 
ትውፊትየተጻፈብቻአይደለም 
ፊልጵ 4:9 "ከእኔየተማራችሁትንናየተቀበላችሁትንየሰማችሁትንምያያችሁትንምእነዚህንአድርጉ፤የሰላምምአምላክከእናንተጋርይሆናል።" 

ሐዋርያትንሐዋርያትካሰኟቸውነገሮችአንዱየጌታችንሐዋርያትበመሆናቸውከጌታችንየተቀበሉትትውፊትነው።ይህንንትውፊትበአካልተገኝተውየዓይንምስክሮችምሆነውተቀበሉመሰከሩም 
1ኛዮሐ 1:1 "ስለሕይወትቃልከመጀመሪያውየነበረውንናየሰማነውንበዓይኖቻችንምያየነውንየተመለከትነውንምእጆቻችንምየዳሰሱትንእናወራለን" 
እንዳለነባቤመለኮትዮሃንስ 

ውንጌላዊውቅዱስሉቃስቅዱሳትመጻሕፍትንለመጻፍምንጩትውፊትነበር። 
ሉቃ 1:1 "ከመጀመሪያውበዓይንያዩትናየቃሉአገልጋዮችየሆኑትእንዳስተላለፉልን፥በኛዘንድስለተፈጸመውነገርብዙዎችታሪክንበየተራውለማዘጋጀትስለሞከሩ" 

ሐዋርያትበጽሑፍምበቃልምአስተምረዋል። 
2ኛዮሐ1:12 "እንድጽፍላችሁየምፈልገውብዙነገርሳለኝበወረቀትናበቀለምልጽፈውአልወድም፥ዳሩግንደስታችሁፍጹምእንዲሆንወደእናንተልመጣአፍለአፍምልናገራችሁተስፋአደርጋለሁ።" 
ሐዋርያውቅዱስዮሃንስበጽሑፍያስተማረውእንደሚገኘውሁሉበቃልያስተማረውምበቤተክርስቲያንውስጥይገኛል። 

ሐዋርያውቅዱስጳውሎስበመልእክቱከጻፈውበተጨማሪበአካልተገኝቶየደነገገውአለ 
1ኛቆሮ 11:34 "ማንምየራበውቢኖርለፍርድእንዳትሰበሰቡበቤቱይብላ።የቀረውንምነገርበመጣሁጊዜእደነግጋለሁ።" 
ይህበቃሉየደነገገውነገርወዴትአለ ? በቤተክርስቲያንትውፊትይገኛል። 
ሁሉምነገርበመጽሐፍቅዱስውስጥአልተጻፈም 
ዮሐ 20:30 "ኢየሱስምበዚህመጽሐፍያልተጻፈሌላብዙምልክትበደቀመዛሙርቱፊትአደረገነገርግንኢየሱስእርሱክርስቶስየእግዚአብሔርልጅእንደሆነታምኑዘንድ፥አምናችሁምበስሙሕይወትይሆንላችሁዘንድይህተጽፎአል።" 
ጌታችንበወንጌል "ሰማይእናምድርያልፋሉቃሌግንአያልፍም" በማለትአስተምሮናልበማቴ 24:35።ታዲያበወንጌልሳይጻፍየቀረውትምህርቱጠፋን? ፈጽሞአልጠፋም።በቤተክርስቲያንትውፊትውስጥአለ። 

ሐዋርያትበጽሑፍያገኙትንብቻሳይሆንበትውፊትሳይጻፍያገኙትንምተምህርትተጠቅመውበታል። 
1ኛቆሮ 9:14 "እንዲሁደግሞወንጌልንየሚሰብኩከወንጌልቀለብእንዲቀበሉጌታደንግጎአል።" 
ይህበትውፊትየተገኘእንጂበአራቱወንጌላትአልተመዘገበም።

 

4901 W Indian School Rd

Phoenix, AZ 85031

(602) 328-0992

  • Facebook Social Icon