top of page

This is a great place to tell people more about yourself and peak their interest.

For more info, they can follow you on social in a click.

  • White LinkedIn Icon
  • White Twitter Icon
  • White Google+ Icon

ነገረ መላአክት

       ትርጕም

ጥሬ ቃሉን ስንመለከተው መልአክ የሚለው የግእዝ ቃልኹለት ትርጉሞች አሉት፡፡አንደኛው አለቃ፣ ሹም ማለት ነው፡፡ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የምናገኛው ሰባቱ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች መላእክት ተብለው መጠራታቸውም ከዚኽ አንጻር ነው /ራዕ. 2 እና 3/፡፡ኹለተኛውና ከተነሣንበት ርእስ አንጻር ስናየው ደግሞ መልክእተኛ፣ የተሰደደ፣ የተላከ የሚል ትርጕም አለው /ዕብ.1፡14/፡፡ ይኸውም የመላእክት ተግባርምን እንደኾነ የሚያስረዳ ቃል ነው፡፡መላእክት ከእግዚአብሔር ወደሰው፥ ከሰውም ወደ እግዚአብሔር የሚላላኩ መናፍስት ናቸውና፡፡መላእክት በሌላ ስማቸው የሰማይ ሠራዊት ተብለው ይጠራሉ፡፡

       መላእክት ስንት ወገን ናቸው?

መላእክት ኹለት ወገን ናቸው፡፡ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የኾነው የዲያብሎስ ሠራዊት የኾኑት እኩያን መላእክት፡፡ ስለዚኽ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡

       መላእክት መቼ ተፈጠሩ?

መላእክት የተፈጠሩት በመዠመሪያው ቀን ነው /ኩፋ.2፡7-8/፡፡መዝሙረኛው ክቡር ዳዊትም ይኽን በማስመልከት፡- “በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተፈጠሩ፤ የሰማይ ሠራዊትም ኹሉ በአፉ እስትንፋስ” ይላል /መዝ.32፡6/፡፡ምንም እንኳን በመዠመሪያው ቀን የተፈጠሩ ቢኾኑም ግን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሰባቱ ሰማያት በኋላ በ9ኛው ሰዓተ ሌሊት ነው የተፈጠሩት፡፡ ይኽ ለምን እንደኾነ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አክሲማሮስ በተባለ መጽሐፉ ላይ፡- “በፊት ፈጥሯቸው ቢኾን እኛም አብረነው ፈጠርን ፤ያዝንለት ፤ተራዳነው ባሉ ነበር ፡፡አንድም ርሱ ቢመሠርት እኛ ገነባን ፤ርሱ ቢገነባ እኛ መሠረትን ባሉ ነበር፡፡ ይኽም ሳጥናኤል በኋላ እኔ ፈጠርኳችኁ እንዳለው ማለት ነው” በማለት ያብራሯል /አክሲማሮስ ዘእሑድ፣ገጽ 24/፡፡

አንዳንድ ሊቃውንት መላእክት ከሰው በፊት ስለተፈጠሩ የሰው ታላላቅ ወንድሞችናቸው ይሏቸዋል፡፡ ተፈጥሮአቸውም ካለመኖር ወደ መኖር ነው፡፡ መላዕክት እንደ እሳት የሚሞቁ፣ እንደነፋስ የሚረቁ ስለ ኾነ  /ዝኒከማኁ/ አንድም እንደ እሳት እንደ ነፋስ ፈጣኖችና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ ኃያላን ስለኾነ ባሕርያቸውን ለመግለጥ ከነፋስና ከእሳት ተፈጠሩ ይባላሉ /መዝ.103፡4፣መዝሙረ ዳዊት ንባቡ ከነትርጓሜው፣ገጽ 489 /፡፡

       የመላእክት አሰፋፈራቸው እንዴት ነው?

የመላእክት ቁጥራቸው ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አያውቀውም /ዳን.7፡10/፡፡በነገድ በነገድ ስናያቸው ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እንደሚነግረን 100 ነገዶች ናቸው፡፡እያንዳንዱ ዐሥር ዐሥር ነገድ የሚይዙ ሲኾኑ ቅደም ተከተላቸውም ይኸው ነው፡- አጋዕዝት /አለቃቸው ሳጥናኤል (ሰማልያል) የአኹኑ ዲያብሎስ ነው/፣ኪሩቤል /አለቃቸው ኪሩብ ነው፤ አራት ራስ አራት ገጽ አላቸው፡፡ ገጻቸውም ገጸ ሰብ እገጸ አንበሳ ይመስላል፡፡ ሰውነታቸው ኹሉ በዓይን የተሸለመ ሲኾን ዓይናቸውም እንደነብር ቆዳ ዥንጕርጕር ነው /ሕዝ.1፡6-7፣ 18-19/፡፡አገልግሎታቸው በቀሳውስት አምሳል የሥላሴን ዙፋን መሸከምነው/፣ሱራፌል /አለቃቸው ሱራፊ ነው፤በዲያቆናት አምሳል ለጸሎት የሚተጉና የሚያተጉ የምስጋና መላዕክት ናቸው ፡፡ገጻቸው ገጽን ስር ገጸ እንስሳ ይመስላል፡፡ ስድስት ስድስት ክንፍ አላቸው ኢሳ.6፡2-3/፣ኃይላት /አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው  /ኄኖክ.10፡2-10/፡፡የሥላሴ ሰይፍ ጃግሬዎች ናቸው/፣አርባብ /አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በሥላሴ ፊት በአጋፋሪ በአስተናጋጅ አምሳል የሚቆሙ ናቸው ኄኖክ  10፡7-8፣ ሉቃ.1፡19/፣ መናብርት /አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በጋሻጃግሬ አምሳል ያገለግላሉ፡፡ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ዘለዓለም እንደነፋስ ሲበሩ ይኖራሉ /፣ሥልጣናት /አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው ፡፡የሥላሴ አዋጅ ነጋሪዎችና መላዕክትን በየጊዜው ለጸሎትና ለምስጋና የሚያተጉናቸው /፣መኳንንት /አለቃቸው ሰዳካኤል ይባላል፡፡የሥላሴ ቀስተኞች ናቸው፡፡ተራራ የሚንድ፣ ድንጋይ የሚሰነጥቅ ፣የእሳት ፍላፃ የእሳት ቀስት ይዘው ሰውን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሲጠብቁ ይኖራሉ፡፡በትንሣኤ ዘጕባኤ ጊዜ የሰውን ኹሉ አጥንት ሰብስበው ለትንሣኤ የሚያበቁ እንዚኽ ናቸው ማቴ.24፡31-42/፣ሊቃናት /አለቃቸው ሰላታኤል ይባላል፡፡የሥላሴ ፈረስ ባልደራስ ናቸው፡፡የእንስሳት ጠባቂ መላዕክት ናቸው /፣መላዕክት /አለቃቸው አናንኤል ይባላል፡፡እንደ ብረት የጸና የእሳት ነጐድጓድን ወደ ምድር የሚወነጭፉ፣ ፀሐይን ጨረቃን ከዋክብትን አዝርዕትን አትክልትን ዕፅዋትን ከምድር በላይ ከሰማይ በታች የተፈጠሩትን የሚጠብቁ ናቸው ኩፋሌ 2፡6-8/፡፡

እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት የሚኖሩባቸው ቦታዎች ሦስት ሲኾኑ ኢዮር ራማ እና ኤረር ይባላሉ ፡፡ የመዠመሪያዎቹ 40 ነገድ በኢዮር፣ ቀጣዮቹ 30 በራማ፣ የመጨረሻዎቹ 30ም በኤረር የሰፈሩ ናቸው፡፡ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከተዋረደ በኋላ ግን የነገደ መላእክቱ ቁጥር ከ100 ወደ 99 የአለቆች ቁጥርም ከ10 ወደ 9 ተቀንሷል፡፡እነዚኽ መላዕክት ለተልዕኮ ፈጣሪ ካላዘዛቸው በቀር ከስፍራቸው አይለቁም፡፡ ሲያዛቸው ግን ወደ ላይ እስከጽርሐ አርያም ወደታች እስከ በርባሮስ ድረስ ከብርሃን ፍጥነት በላይ በኾነ ቅጽበት ይወጣሉ ፤ይወርዳሉ ፡፡የመላእክት ባሕርይ እንዴት ነው?

የመላእክት ባሕርይ ከሰው ጋር የሚያመሳስለውም የሚያለያየውም ነጥብ አለው፡፡ ከሰው በምን ይለያሉ ቢሉ መላእክት፡- ረቂቃን ናቸው፡፡ ከነፋስ ነፍስ ትረቃለች፤ ከነፍስ መላእክት ይረቃሉ፤ ከመላእክት ደግሞ ሥላሴ ይረቃሉ፡፡

· እንደሰው አይራቡም፤ አይጠሙም፡፡ ልብስ፣ መጠለያ አይፈልጉም፡፡  “እኔም ተገለጥኩላችኁ፤ ነገር ግን እይታን አያችኁ እንጂ ከእናንተ ጋር አልበላኹም ፤አልጠጣኹምም” /ጦቢት 12፡19/፡፡

· የመላዕክት ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና መጠጣቸውም የመለኮት ፍቅር ነው፡፡

· መላዕክት ፆታ የላቸውም /ማቴ.22፡30-31/፡፡በመኾኑም አይጋቡም፤ አይዋለዱም፡፡

· ስለነገ አይጨነቁም፡፡

·መላዕክት ከዝንጋዔ የራቁ ፣ባለአዕምሮ የኾኑ፣ ዕውቀት ያላቸው፣ ይዋኄንና ትዕግሥትን ገንዘብ ያደረጉ ፣ለዘለዓለም የማይነጥፍና የማያቋርጥ ይልቁንም ዘወትር እንደዥረት ውኃ የሚወርድ ምስጋና ያላቸው ናቸው  /ሥነፍጥረት፣

·ምንም እንኳን ከሰው በፊት ቢፈጠሩም አያረጁም፡ ፡ዘወትር ውቦች፣ ብርቱዎችና ውርዙዋን ናቸው፡፡

· ኢ-መዋትያን ናቸው (አይሞቱም) /ሉቃ.20፡36/፡፡ይኸውም ልክ እንደ እኛ ነፍስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ነው፡፡

· እንደ ሰው አንድ ጊዜ ደግ ሌላ ጊዜ ክፉ በመሥራት አይዋልሉም፡፡

        ከሰው ምን ያመሳስላቸዋል ስንል ደግሞ፡-

·ምንም ረቂቃን ቢኾኑም ሕልውና ከአካል ጋር አላቸው፡፡ ዮሐንስ ዘደማስቆ የተባለ አባት ይኽን ሲያብራራው ፡- “መላእክት ረቂቃን ናቸው የምንላቸው ከእኛ አንጻር ነው፡፡ ከማንም ጋር ከማይነጻተረው ከእግዚአብሔር አንጻር ሲታዩ ግን ግዙፋን ናቸው፡፡ ፍጹም ረቂቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውና” ብሏል፡፡

·ምንም ረቂቃን ቢኾኑም ውሱናን ናቸው፡፡ እንደሰው በቦታ የሚገቱ ባይኾኑም መጠን አላቸው፡፡ መጠናቸውና አርዐያቸውም የተለያየ ነው፡፡ ቁመታቸው ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ መላዕክት አሉ፡፡በክንፋቸው ብቻ አንድ አገር የሚያለብሱ መላዕክት አሉ፡፡ ራሳቸው ብቻ ተራራ የሚያክሉ መላዕክት አሉ፡፡ በዓይን የተቀረፁ የተሸለሙ ኹለንተናቸው ዓይን የኾነ መላዕክት አሉ፡፡ ስድስት ክንፍ ያላቸው መላዕክት አሉ፡፡ መብረቅ ለብሰው መብረቅ ተጐናጽፈው የሚኖሩ መላዕክት አሉ ፡፡ ነፋስ ለብሰው ነፋስ ተጐናጽፈው የሚኖሩ መላዕክት አሉ፡፡ብሩህ ደመና ጠምጥመው የሚኖሩ መላዕክት አሉ፡፡እግራቸው ዓምደ እሳት የሚመስል መላዕክት አሉ ፡፡ የእነዚኽን መላዕክት አርዓያቸውን መጠናቸውን ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቀው የለም /ኩፋ.2፡7-8/፡፡

·ዐዋቂዎች ናቸው፡፡ ዕውቀታቸው ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደተናገረው ከሰው እጅግ ከፍ ያለ ነው /2ኛጴጥ.2፡11/፡፡ ምንም ከሰው እጅግ ከፍ ያለቢኾንም ግን ዕውቀታቸው መጠን አለው ፡፡ከእግዚአብሔርን በቀር ፍጹም ዕውቀት ያለው የለምና ፡፡ እኛ ዕውቀታችን እንደመላእክት የሚኾነው ከትንሣኤ ዘጕባኤ በኋላ ነው /1ኛቆሮ.13፡12/፡፡ · ነጻ ፈቃድ አላቸው፡፡

· እንደሰው ባሕርያቸውን የሚገልጽ ስም አላቸው፡፡

ሰው ከመበደሉ በፊት ልክ እንደመላእክት ንጹሕ፣ ውብና ብርቱ ነበር፡፡በፍጥረታት ላይ ሥልጣን ነበረው፡፡ርሱሲበድል ግን ከሥልጣን የወረደ ሰው እንደ ድሮ የሚያከብረው እንደሌለ ኹሉ ፍጥረታቱ አዳምን አልታዘዝ አሉት፡፡ እንደዉም ተበረታቱበት፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣውም ወደ ቀድሞ ክብራችን ወደልጅነት ወደቀድሞ ቦታችን ወደገነት ከዚያም በላይ ወደመንግሥተ ሰማያት ሊመልሰን ነው፡፡በመኾኑም ሰውምንም እንኳን በዚኽ ዓለም ሳለ ብዙ ውጣ ውረዶችን ቢያሳልፍም በመጨረሻ መላእክትን ይመስላል፡፡ ለዚኽም ነው ቅዱሳን መላእክት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ.1፡14 ላይ እንደገለጸው ታናሽ ወንድማቸውን ሰውን በማገልገል ላይ ያሉት፡፡

       የመላእክት ትክክለኛ ስም ይታወቃልን?

ምንም እንኳን በስም በስም ብንጠራቸውም ስማቸው ነገረ እግዚአብሔርን የሚያስረዳ እንደኾነ እንጂ በቅጥነተ ኅሊና ስናስተውለው ማን ማን እንደሚባሉ አይታወቁም ፤ስም የሌላቸው ኾኖ ሳይኾን የሰው አዕምሮ ሊረዳው አይችልም፡፡ ለምሳሌ ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነው፡፡ ይኽም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትን የሚገልጽ እንጂ የመልአኩ ትክክለኛ ስም አይደለም ፡፡ሚካኤል ማለት መኑ ከመ እግዚአብሔር ማለት እንጂ የመልአኩ ስም አይደለም ፡፡በነገራችን ላይ የእግዚአብሔር ትክክለኛ ስሙም አይታወቅም፤ የለውም ማለት ሳይኾን ኹለንተናውን የሚገልጽ ስም በሰው ቋንቋ መግለጽ አይቻልም፡፡

       መላእክት መልክ አላቸውን?

በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን መላእክት በተለያየ መልክ እንደተገለጹ እናነባለን፡፡ለምሳሌ፡-

· በእሳት አምሳል /ዘጸ.3፡2-4/፤ለሙሴ፤

· በዓምደ ብርሃንና ደመና አምሳል /ዘጸ.13፡21፣ 23፡20-21፣ዘኅ.20፡16/፤ለሕዝበ እስራኤል፤

· በተራ ሰው አምሳል /መሳ.6፡12-23/፤ለጌድዮንና ለጦቢት፤

· በነቢይ አምሳል /መሳ.13፡6/፤ለማኑሄ ሚስት፤

· በእሳት ፈረስና ሰረገላ አምሳል /2ኛነገ.6፡16-17/፤ለኤልሳ ዕሎሌ፤

· በእሳት አምሳል  /ሕዝ.8፡2/፤ለነቢዩ ሕዝቅኤል፤

· በፍታ እንደለበሰ ፣ወገቡም በወርቅ እንደታጠቀሰው /ዳን.10፡5/፤ለነቢዩ ዳንኤል፤

· ልክ እንደ ትሑት ሰው /ሉቃ.1፡12-13/፤ለዘካርያስና ለእመቤታችን፤

· የጌታ ክብር በዙርያቸው ኾኖ  /ሉቃ.29-30/፤ ለእረኞች፤

ይኽም ማለት መላእክቱ ሰው እንዲገባው በሰው አእምሮ መጠን ተገለጡ ማለት እንጂ መልካቸው ተለዋዋጭ ነው፤ የራሳቸው የኾነ ቋሚ መልክም የላቸውም ማለት አይደለም፡፡የመላእክት ተግባር ምንድነው?

የመላእክት ተግባር እንደሚከተለው ማየትይቻላል፡-

· ያለማቋረጥ እግዚአብሔርን  “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ ያመሰግናሉ /ኢሳ.6/፤

·የእግዚአብሔርን መልካም ዜና ወደሰው ያመጣሉ፡፡ይኸውም ለአጋር፣ ለአብርሃም፣ ለሐና እመ ሳሙኤል፣ለካህኑ ዘካርያስ ለእመቤታችን እንዳመጡላቸው ማለት ነው፡፡

·ማስተዋልንና ጥበብን ለሰው ልጆች ያድላሉ፡ ፡ይኸውም ቅዱስ ገብርኤል ለነቢዩ ዳንኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልም ለዕዝራ እንዳደረጉት ማለት ነው፡፡  

· ሰውን ከጥፋት ያድናሉ፡፡ ይኸውም ሎጥን ከሰዶምና ጐመራ ሰዎች ጋር እንዳይጠፋ /ዘፍ.19/፣ሠለስቱ ደቂቅን ከሚነድ እሳት እንዳዳኗቸው ማለት ነው /ዳን.3፡12-30/፡፡መዝሙረኛው ክቡር ዳዊት፡- “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ፤ ያድናቸውማል” /መዝ.34፡7/፤ በሌላ ቦታም  “ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም መቅሰፍትም ወደቤትህ አይገባም፡፡ በመንገድህ ኹሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዝዛቸዋልና፡፡ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሱኻል” ያለውም ስለዚኹ ነው /መዝ.91፡10-12/፡፡

·የሰውንም መልእክት ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡ የሰውን መልእክት ወደእግዚአብሔር ያደርሳሉ ሲባል ምን ማለት እንደኾነ የቆጵረሱ ሊቀ ጳጳስ ሊቁ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ መጽሐፉ ላይ፡-“ (የካህናተ ሰማይ ማዕጠንት) የጻድቃን ጸሎት፤የሰማዕታት ገድል፤ የደጋግ ሰዎች ምግባር ነው” ብሎ ያብራሯል  /መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ገጽ 51/፡፡

·የእግዚአብሔርን ቁጣ ወደሰዎች ያመጣሉ፡፡ እነርሱም የመዓት መላእክት የሚባሉ ሲኾኑ በትዕቢቱና በክፋቱ ከሥልጣኑ የወረደው የዲያብሎስ ሠራዊትየነበሩና በኋላ ግን አለቃቸው ሲክድ ያልካዱ በእምነታቸው የፀኑ ከሣጥናኤል ሠራዊትነት ተለይተው ከነቅዱስ ሚካኤልና ከነቅዱስ ገብርኤል ጋር የተደመሩት ናቸው፡፡ እነዚኽ የመዓት መላእክት እጅግ ቁጡዎችና ቀናተኞች ናቸው፡፡

       ጠባቂ መልአክ

ክቡር ዳዊት “ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም መቅሰፍትም ወደቤትህ አይገባም ፡፡ በመንገድህ ኹሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፡፡ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሱኻል”  እንዳለው /መዝ.91፡10-12/ እያንዳንዱ ሰው ጠባቂ መላእክት እንዳሉት ያስረዳል፡፡ እስራኤል ዘሥጋን የጠበቃቸው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይኽንንም ለኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ነግሮታል  /ኢያ.5፡14-15/፡፡ይሁዳም የመልአኩ ስም ማን እንደኾነ በግልጽ ነግሮናል /ይሁዳቁ.9/፡፡

አስቀድመን እንደተመለከትነው ለእያንዳንዱ ሰው ብቻሳ ይኾን ለእንስሳት፣ ለዕፅዋት፣ለምድር፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ለከዋክብት፣ ከምድርም በታች ለተፈጠሩ ፍጥረታት በሙሉ ጠባቂ መላእክት አሏቸው፡፡ለምሳሌ እንስሳትን የሚጠብቀው መልአክ ሰላታኤል ይባላል፡፡አናንኤል የሚባለው ነገደ መላእክት ደግሞ እንደብረት የጸና የእሳት ነጐድጓድን ወደ ምድር የሚወነጭፉ፣ ፀሐይን ጨረቃን ከዋክብትን አዝርዕትን አትክልትን ዕፅዋትን ከምድር በላይከ ሰማይ በታች የተፈጠሩትን የሚጠብቁ ናቸው  /ኩፋሌ 2፡6-8/፡፡

ቅዱስ ባሲልዮስ ዘቂሳርያ ሰውን ስለሚጠብቁ መላእክት ሲናገር፡-  “ክፉ ሥራ ካልሠራን በቀር ጠባቂ መልአካችን ከእኛ አይለይም፡፡ ጭስ ንብን ከቀፎው እንዲወጣ እንደሚያደርገው ኹሉ የእኛ ኃጢአትም ጠባቂ መልአካችን ከእኛ እንዲለይ ያደርጓል”  ብሏል፡፡

መላእክት - የቤተክርስቲያንአገልጋዮችናቸው!!!

ቅዱሳን መላእክት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ብልት ናትና መላእክትም ቤተክርስቲያንን ያገለግላሉ፡፡ የጌታችንን ሰው መኾን ያበሰሩን መላእክት ናቸው፡፡ በቤተልሔም ግርግም ሲወለድ እጅግ ደስ ብሏቸው ያመሰገኑት መላእክት ናቸው፡፡ ስለልደቱ ለእረኞች የነገሯቸው መላእክት ናቸው፡፡ ወደ ግብጽ ሲሰደድ አብረዉት የሔዱ መላእክት ናቸው፡፡በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በሔደ ጊዜ ያገለገሉት መላእክት ናቸው፡፡ ጌታችን በጌተ ሴማኒ የአታክልት ስፍራ ሲጸልይ ሲያበረቱት የነበሩት መላእክት ናቸው፡፡አይሁድ ሊሰቅሉት ሲሉ ቸርነቱ ከልክሏቸው እንጂ አይሁድን ለማጥፋት የተዘጋጁት መላእክት ናቸው፡፡ ደሙን ወደዓለም ኹሉ የረጩት መላእክት ናቸው፡፡ ትንሣኤውን ያበሠሩን መላእክት ናቸው፡፡ ሲያርግ ደግሞም ዳግም እንደሚመጣ የነገሩን እነዚኽ መላእክት ናቸው፡፡ ዳግም ሲመጣ አብረዉት የሚመጡትና ሙታንን የሚቀሰቅሱትም እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡

ይኽ አገልግሎታቸው በሐዋርያትም የተመለከትነው ነው፡፡ሊቀ ካህኑ ሐዋርያቱን ሲያስራቸው ሰንሰለታቸውን የፈቱላቸው መላእክት ናቸው /ሐዋ.5፡17-20፣ 12፡7-10/፡፡የገሊላው ንጉሥ ይሁዳ ሐዋርያው ያዕቆብን ከገደለው በኋላ ጴጥሮስንም ሊገድለው ሲል በትልተበልቶ እንዲሞት ያደረጉት መላእክት ናቸው /ሐዋ.12፡23/፡፡ፊሊጶስ በሰማርያ እያስተማረ ሳለ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን አስተምሮ እንዲያጠምቀው የነገሩት ቅዱሳን መላእክት ናቸው /ሐዋ.8፡26/፡፡ ሐዋርያትን እየመሩ፣ አሕዛብንም እያዘጋጁ ወንጌል በአሕዛብ አገር እንዲስፋፋ ያደረጉት ቅዱሳን መላእክት ናቸው  /ሐዋ.10/፡፡ እነቅዱስ ጳውሎስ መርከብ በአውሎ ነፋስ ቀንና ሌሊት ስትናወጥ አንዲት ነፍስ እንኳን እንደማትጠፋ ያጽናኗቸው ቅዱሳን መላእክት ናቸው /ሐዋ.27፡20-25/፡፡በአጠቃላይ ቅዱሳን መላእክት ከክርስቶስ ደግሞም ብልቱ ከምትኾን ከቤተክርስቲያን  (ይኸውም ከእኛ ከምእመናን) አይለዩም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን እጅግ አድርጐ ይወዳል፡፡ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትንም ጠባቂ አድርጐ ይልክላቸዋል፤ ይልክልናል፡፡

በሥራችን ኹሉ ለሚጠብቁን፣ ዘወትር በኃጢአት ስንወድቅ ደግፈው ለሚያነሡን፣ በኃጢአት ስንጨማለቅ “ለዛሬ ተዋት” እያሉ ስለእኛ መዳን ፈጣሪን ለሚማልዱልን /ሉቃ.13፡7-9/፣በእኛ ንስሐ መግባት ስለእኛ በሰማያት ድል ያለምስጋና ለሚያቀርቡ /ሉቃ.15፡7/፣ እንቅፋት እንዳይመታን ለሚጠብቁን፣ በርኵሳን መናፍስት አንድም በፈቃደ ሥጋችን ላይ እንድንሠለጥን ለሚራዱን ለእነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ውለታ ታድያ እንዴት መክፈል ይቻለናል? እነዚኽን ጠበቃዊቻችን ለሰጠን እግዚአብሔርስ ተመስገን ከማለት በቀር ምን ማለት እንችላለን? በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ለዘለዓለም እስከዘለዓለም ድረስ ለአምላካችን ይኹን አሜን /ራዕ.7፡12/፡፡

ነገረ መላአክት

የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት

ቅዱሳን መላእክት ንጹህ ክቡርና ዘወትር የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው::  ዘወትር በእግዚእብሔር ፊት ይቆማሉ የሰዎችን ጸሎትና ልመና፥ ምስጋናና ውዳሴ ወደ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ብስራት፥ምህረትና ቸርነት ወደእኛ ዘንድ ያመጣሉ:: እንዲሁም ቁጣና መአት ለወንበዴዎችና ለአመጸኞች ይሰጣሉ::

‹‹የእግዚአብሔር ልጆች  (መላእክት)  በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፡፡ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ›› ይለናል (ኢዮ1.6)፡፡

‹‹ለመቆም›› ሲል ለመለመን፣ ለማማለድ ማለት ነው፡፡ አብሮአቸውም ሰይጣን መምጣቱን ልብ በል፡፡ሰይጣን የመጣው ለምን ነበር? ጻድቁ ኢዮብን ለመፈተን ፈቃድ ያገኝ ዘንድ ፈጣሪውን ለመለመን አልነበረምን? የመላእክትም አመጣጥ ፈጣሪቸውን ስለሰው ለመለመን እንጂ ለሌላ አልነበረም ፡፡ ይህን ሲገልጥ ‹‹ለመቆም መጡ›› ይለናል፡፡ መቆም መለመን፣ ማማለድ ማለት ነውና፡፡መቆም ማለት መጸለይ፣ ማማለድ የሚል ፍቺ እንዳለው ካስጨበጡ በኋላ ይህንን ቃል በመጠቀም የመላእክትን አማላጅነት ማስረዳት ቀላልይሆናል፡፡

‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ፡ ፡›› ሉቃ 1:19

በማለት ተናግሯል፡፡ይህም በቅዱስ ወንጌል የተጻፈ ኃይለ ቃል ሲሆን አብዛኞቻንን እናውቀዋለን፡፡ ልዩ የሚሆነው ግን የቃሉን ትክክለኛ አገባባዊ ትርጉም ባለማወቃችን ምክንያት መልአኩ ይህን ባለጊዜ ‹‹እኔ አማላጅ ነኝ›› እንዳለን አድርገን አለመረዳታችን ነው፡፡ መቆም ማለት ማማለድ የሚል ትርጉም ካለው ‹‹በእግዚአብሔር ፊትየ ምቆም ›› ማለት ደግሞ ‹‹የማማልድ›› ማለት መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱን ራሱ ግልጽ በሆነ መንገድ ነግሮናል ማለት ነው፡፡

በዚህ ስፍራ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅ ነኝ ማለቱን ካላመንን  ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ማለቱን ምን ብለን እንረዳዋለን? የእግዚአብሔር ፊቱ ወደሁሉም አቅጣጫ ነው እንጂ እንደ ፍጡር ወደአንድ ገጽ የተወሰነ አይደለም፡፡ መላእክት ደግሞ በተፍጥሯቸው እንደሰው ልጅ የሚታጠፍና የሚዘረጋ እግረ ሥጋ ስለሌላቸው አይቀመጡም፤ አይተኙምም፡፡ታዲያ አማላጃችሁ ነኝ ማለቱ ካልሆነ በቀር መልአኩ  ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ሲል ምን ማለቱ ነው? መልአኩ እግዚአብሔርን እንደምድራዊ ንጉሥ ራሱን ደግሞ እንደ ንጉሥ ወታደር ቆጥሮ በንጉሡ ፊት ቀጥ ብዬ የምውል ዘበኛነኝ ማለቱ ነውን?  በፍጹም አይደለም ፡፡በእግዚአብሔር ቤት ደጅ አፍ መቆምና በእግዚአብሔር  ፊት መቆም ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ምሥጢራቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ (ራእ21.12፤ዘፍ3.24) ይልቅ ሊሆን የሚችለው እኔ በፊቱ ባለሟልነት ያለኝ ሁሉ ጊዜ ስለእናንተ የማማልድ ነኝ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

መልአኩ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ለምንድንነው? ለማመስገንነው እንዳንል ይህንን ሐሳብ ለካህኑለዘካርያስ መንገር ለምንአስፈለገው? የሚል ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ትርጉሙ እንዲህ ቢሆን ወደካህኑ ወደ ዘካርያስ ከመጣበት ጉዳይ ጋር ንግግሩ ምንም ግንኙነት አይኖረውምና ይህን መናገር አያስፈልገውም፡፡ ከዚህይልቅ እኔ ሰዎችን ሁሉ ለማማለድ በእግዚአብሔር የምቆም ባለሟልነት ያለኝ መልአክ በመሆኔ የለመንከው ልመና መድረሱን የምሥራች ልነግርህ ብመጣ ቃሌን እንዴት ትጠራጠራለህ?  ለማለት ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመውመልአኩ ገብርኤል ነኝ›› በማለት መልአኩ ይህን ተናገረ ብንል ከሁሉ በላይ የሚያስኬድና ለአእምሮ የሚመች ትክክለኛ ትርጓሜ ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ስለቅዱስ ሚካኤልም በትንቢተ ዳንኤል ላይ እንዲህ ተጽፏል፡፡ ‹‹በዚያ ወራት ስለሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› ይላል፡፡ (ዳን12.1)

በዚህ ጥቅስ ቅዱስ ሚካኤል  ‹‹ስለሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ተብሏል፡፡እረ ለመሆኑ ቅዱስ ሚካኤል ስለሰዎች በእግዚአብሔር ፊት  ‹‹የሚቆመው›› ለምንድርነው? ለማማለድ አይደለምን? ይህን ካልተቀበልን ቃሉን ምን ብለን እንተረጉመዋለን? ለማመስገን ይቆማልእንዳንል ቃሉየ ሚለው ‹‹ስለሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ነው፡፡ስለእኛ ጥብቅና ይቆማል እንዳንል ወደባሰ ስሕተት ይወስደናል፡፡ ሚካኤል በእግዚአብሔር ፊት ጥብቅና አይቆምምና፡፡ እግዚአብሔርም በጠበቃ የሚሟገቱት አምላክ አይደለምና፡፡ ጥብቅና ይቆማል ከማለት ይልቅ ትክክለኛውና የሚስማማው ወደ ፈጣሪ ሊለምንልን ወይም እኛን ለማማለድ ይቆማል የሚለው ትርጓሜ ነው፡፡ አስቀድሞ እንደተመለከትነው ‹‹መቆም›› የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም አለውና፡፡

ይህ ለምሳሌ ያህል ተጠቀሰ እንጂ በፈጣሪ ፊት እልፍ አእላፋት መላእክት ለምልጃ ይቆማሉ ፡፡ቅዱስ ዳንኤል ‹‹ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፡፡ እልፍ አእላፋትምበ ፊቱ ቆመው ነበር፡፡›› በማለት የገለጸው ይህንን እውነት ነው፡፡ (ዳን7.9-11) ከዚህ በላይ ከብሉይ ስለቅዱስ ሚካኤል ከሐዲስ ደግሞ ስለቅዱስ ገብርኤል የተጻፉት ለማስረጃነት ተጠቅሰዋል፡ ፡የተማሩትንና ያነበቡትን በልብ ለመክተብ መላልሶ ማንበብና ማጥናት እንደሚያስፈልግ እሙን ነው ፡፡ይህን ለማድረግ ብትሻ የቅዱስ ገብርኤል ዝክረ በዓል ወር በገባበ አሥራ ዘጠኝ እንደሚውል ታውቃለህ፡ ፡ስለእርሱም የተጠቀሰው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1.19 መሆኑን ልብ በልና ጥቅሱ ከወርኃዊ በዓሉ ጋር ያለውን ዝምድና መርምር፡፡ማለትም ቁጥር  19 ላይ መጻፉን አስተውል፡፡ ስለቅዱስ ሚካኤልም እንዲሁ አድርግ፡፡ ጥቅሱ በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ  12 ላይ ይገኛል፡፡

 

መላእክት ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ

 

"የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረና ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ መላእክት መካከል አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ::"ጦቢ 12:15

"እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክትፊት ደስታ ይሆናል።"ሉቃ 15:10

"መልአኩም አለው።ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ ።"ሐዋ 10:4

የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት

ለመላእክት የአክብሮት ስግደት ይገባል

· ለቅዱሳት መላእክት የምናቀርበው ስግደት የጸጋ ስግደት ነው፡፡የጸጋ ስግደት ስንል እግዚአብሔር የሰጣቸውን ክብርና ሞገስ አምኖ መንበርከክ ነው፡፡ይህም ራስን ለእግዚአብሔር ከማስገባት የሚመነጭ ነው፡፡ይህም የክብር ፣ሀብት ፣መልካም ሥጦታ ፣ዕድል ፈንታ ፣ትምህርት ፣ብዕል ፣ሞገስ የቸርነት ሥራ አለዋጋ የሚሰጥና የሚደረግ ማለት ነው፡፡

 

ሰዶምና ገሞራን በእሳት ለማቃጠል የተላኩት መላእክት ወደ ሎጥ ቤት በገቡ ጊዜ ሎጥ በግምባሩ ተደፍቶ ለመላእክቱ እንደሰገደ ተጽፏል (ዘፍ. 19፥1)፡፡

 

ኢያሱ ወልደ ነዌ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በተገለጠለት ጊዜ በግምባሩ ተደፍቶ ለመልአኩ ሰግዶለታል፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል የተቃውሞ አነጋገር አልተናገረም፡፡   ‹‹የቆምክባት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግር ህአውጣ›› ከማለት በስተቀር (መጽ ኢያሱ 5፥13)፡፡

 

የእሥራአል ንጉሥ የነበረው ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከእሥራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከመሬት ከፍ ብሎ ሰይፉን ዘርግቶ ለተገለጠላቸው ለእግዚአብሔር መልአክ ሰግደውለታል  (ዜናመዋዕልቀዳ 21፥16)፡፡

 

ነቢየ እግዚአብሔር ዳንኤል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአባል ወንዝ አጠገብ በተገለጠበት ጊዜ ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ራሱን ዝቅ አድርጐ በግንባሩ ወድቆ ሰግዶለታል ፡፡በዚሁም ላይየግርማውን አስፈሪነት እና አስደንጋጭነት ጠቅሷል (ዳን. 8፥15)፡፡

 

"እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየሰገደም ፥በግምባሩም ወደቀ። " ዘኁ 22:31

 

"እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድርነው? አለው። "ኢያሱ 5:13

 

"ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ ፥የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፉ።" 1ኛዜና 21:16

 

"ገብርኤል ሆይ ፥ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ ።እኔም ወደቆምሁበት ቀረበ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ እርሱም ፦የሰው ልጅ ሆይ ፥ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደሆነ አስተውልአለኝ ።ዳን 8:15

 

"ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገማኑ ሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥በምድርም በግምባራቸውተደፉ። "መሳፍ 13:20

 

ከላይ የተገለጹት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያስገነዝቡን ለመላእክት ቅዱሳን ሰዎች እንዴት አክብረው እንደሰገዱላቸው ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ  ‹‹የእግዚአብሐርን ቃል የተናገሩአቸሁን ዋሃቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሮ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው›› (ዕብ. 13፥7) እንዳለው የቅዱሳን አባቶቻችንና ሕይወት አኗኗር ዛሬ ለእኛ መመሪያ ሊሆነን ይገባል፡፡ እነርሱ አድርገው የተጠቀሙበትን ሁሉ እኛምእናደርገዋለን ፡፡እነርሱ ለቅዱሳን መላእክት ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት በስግደት እንደገለጹ እኛም እግዚአብሔር ላከበራቸው ቅዱሳን መላእክት ፍቅራችንንና አክብሮታችንን በሥዕላቸው ፊት በመንበርከክ በመስገድ እንገልጻለን፡፡

 

መላእክት ቢገለጡም ባይገለጡም ሕልውናቸው የተረጋገጠ ነውና ክብራቸው ያው ነው፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ሲገለጡ እንጂ ካልተገለጡ ሊሰገድላቸው አይገባም ሊሉ ይችላሉ፡፡ በዓይን ዓይቶ በእጅ ዳብሶ ከማመን ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን እንደሆኑ ጌታችን አስተምል (ዮሐ. 2ዐ፥29)፡፡

 

ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በዓይናቸው ዓይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው ያደረጉትን እና ያመኑትን ለእኛ በማስተላለፋቸው እኛም የእነርሱን ዓይን ዓይን አድርገንማ እነርሱ አይተዋቸው የሰጡትን ክብር እንሰጣቸዋለን፡፡ መገለጣቸውና አለመገለጣቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ያላቸውን ክብር አይጨምረውም አይቀንሰውምና ክብራቸው አንድ ነው፡፡ ስለዚህ ይሰገድላቸው ዘንድ የሚገባ ከሆነ ሲገለጡ ሳይገለጡ የሚል ሁኔታ መፈጠር የለበትም፡ ለእግዚአብሔር በመንፈስ የአምልኮት ስግደት እንደምንሰግድ ሁሉ  (ዮሐ. 4፥24) እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ አብረው ለሚገኙት ቅዱሳን መላእክትም የጸጋ ስግደት በእምነት ማቅረብ ይገባል፡፡ እነርሱም እግዚአብሐር ባለበት ቦታ ሁሉ አሉና፡፡

ለመላእክት የአክብሮት ስግደት ይገባል

እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ‹‹አትስገድልኝ››ራእ.19፥10

·         ‹‹ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።›› ራእ.19፥10

 

አንዳንዶች ተጠራጣሪዎች ደግሞ ለመላእክት ሲገለጡም ሆነ ሳይገለጡ ምንም ዓይነት ስግደት አይገባቸውም በማለት ራእ. 19፥10 (‹‹አትስገድልኝ››) ላይ ያለውን ይጠቅሳሉ፡፡ በመሠረቱ ይህ ጥቅስ ለመላእክት የጸጋ ስግደት መስግድ እንደሚገባን እንጂ መስገድ እንደማይገባን የሚገልጽ አይደለም፡፡

 

ወንጌላዊውና ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ለመልአኩ መስገዱ ሳያውቀው ሳይረዳው ያደረገው ድርጊት እንዳልሆነ እንድናምን ማንነቱና ሕይወቱ ያስገነዝበናል፡፡ ምክንያቱም የጥበብ፣ የማስተዋል፣ የዕውቀት ጸጋን የሚያድል መንፈስቅዱስ አድሮበት እያለ ሳያውቀው አደረገው ብሎ መናገርና ማመን መንፈስቅዱስን እንደመጽረፍ /መስደብ/ ነው፡፡ በመንፈስቅዱስ የተቃኘ ሰው የሚያመልከውንና የሚሠራውን ሁሉየሚያውቅ ነው፡፡

በተለይ ቅዱስ ዮሐንስ አካል ከሕልውና ተገልጾለት ምሥጢረ መለኮትን የተናገረ ታላቅ ሰው ሆኖ ሳለ ትንሿ ጉዳይ ተሰውራው ለመልአኩ ሳያውቅ ሰግዶ ተግሳጽ ደረሰበት ብሎ ማመን ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ክህደት ምጭምር ነው፡፡ የመንፈስቅዱስን ሰላም ማቃለል ነው፡፡  

«መንፈስቅዱስ የሰደበ ደግሞ ኃጢአቱ አይሠረይለትም፡፡» (ማቴ. 12፥31-32)፡፡

 

የመልአኩ አነጋገር ታዲያ እንዴት ይተረጎማል?  መልአኩ ቅዱስ ዮሐንስን አትስገድልኝ ማለቱ ስለሁለት ነገር ነው፡፡

1ኛ. ስለትኀትና

ዲያብሎስ ከሥልጣኑ የተሻረው ከክብሩ የተዋረደው በትዕቢቱ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ቅዱሳን መላእክት ግን ትሕትናን ገንዘብ ያደረጉ በመሆናቸው እንደሰይጣን ስገዱልን የሚሉ አይደሉም፡፡ ዳሩ ግን እግዚአብሔር ይከበሩ ዘንድ ፈቃዱ በመሆኑ የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲወዷቸውና እንዲያከብåቸው አድርጓል፡፡ ለዮሐንስ በሰገደለት ጊዜ «አትስገድልኝ» ማለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላከ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚያወጣ ለጣኦት እንደመስገድ የሚያስቆጥር ሆኖ ሳይሆን መልአኩ ራሱን በዮሐንስ ፊት ዝቅ ከማድረጉ የተነሣ ስለትሕትና የተናገረው ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ሰው አክብሮ እጅ ቢነሣው  /ከመቀመጫው ሲነሳና ሲቀበለው / ረአይገባም እንደሚለው ሁሉ ማለት ነው፡፡ ለዚሁም ማረጋገጫ የሚሆነን  (ለትሕትና የተናገረ መሆኑን) በምዕራፍ 19 የሰጠውን ማስጠንቀቂያ በምዕራፍ 21 ላይ መድገሙ ነው፡፡ ለትሕትና የተናገረው መሆኑን ያወቀው ዮሐንስ ለመልአኩ ክብር መስጠት እንዳለበትና መስገድ እንደሚገባው ዐውቆ ድጋሚ ሲገለጥለት በድጋሚ ሰግዶለታል፡፡

2ኛስለሥልጣነ ክህነት ክብር ሲል

የቤተክርስቲያን የአጥቢያ ኮከብ ቅዱስ ጳውሎስ የካህናትን ሥልጣን አስመልክቶ ሲያስተምር

#  ካህናት ሰውን ሁሉ እንደሚዳኙ አታውቁምን? እናንተ ሰውን ሁሉ የምትዳኙ ከሆናችሁ ይህን ትንሹ ንነገር ልትፈርዱ አይገባችሁምን? የዚህንስ ዓለም ዳኝነት ተውትና መላእክትንስ ንኳ እንድንገዛ አታውቁምን  (1ቆሮ 6፥2-3) ብሏል፡፡

 

ከዚህ ትምህርቱ የምገነዘበው ካህናት በሥልጣናቸው መላእክትንስ ንኳ ሳይቀር እንደሚያዙ ነው፡፡ይህንንም ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት እንረዳለን፡፡በ344 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ የተወለደው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እምነትንና ፍቅርን፣ ትዕግሥትን ናትሕትናን፣ በአንድነት ገመድ አስሮ ሕዝቡን ለ7  ዓመት ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በ387 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ ፖትርያርክነት ተሾሞ ሳለ አንድ ጉዳይ ይገጥመዋል፡፡

 

ንጉሡ አርቃድዮስና ንግሥቲቱ አውዶክያስ ልጅ እየወለዱ እየሞተባቸው አላድግ ስላላቸው የዚህን ምክንያት ቢጠይቁ ደግ ሰው ክርስትና ባያነሣላችሁ ይሆናል ስላሏቸው ከዮሐንስ አፈወርቅ የበለጠ ደግ ሰው በዘመናችን አለን? በማለት ሴት ልጅ በወለዱ ጊዜ መጥተህ ክርስትና አንሣልን ብለው ላኩበት እርሱም ጥሪውን አክብሮ ሲሆድ በመንገድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተላከ መልአክ ጋር ይገናኛል፡፡ የበቃ ነውና ረቂቁን መልአክ ሊያየው ችሏል፡፡ዮሐንስም መልአኩን ‹‹ወዴት ትሄዳለህ?›› ብሎ ጠየቀው መልአኩም ሲመልስለት ‹‹አሁን አንተ የምትሄድባትን ብላቴና ነፍሷን ከሥጋዋ ለይተህ አምጣ ብሎኝ የታዘዝኩትን ለመፈጸም ወደዚያ መሄዴ ነው›› ይለዋል፡፡ ዮሐንስም ‹‹ቆየኝ በጥምቀት ሀብተውልድና፣ ስመክርስትና ከተሰጣት በኋላ የታዘዝከውን ትፈጽማለህ፡፡ እስከዚያው ግን ከዚሁ አትንቀሳቀስ››  ብሎት በሥልጣነ ክህነቱ ገዝቶት ሄደ ፡፡ መልአኩም የዮሐንስን ግዝት ጠብቆ ባለበት ቆመ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ልጅቷን ካጠመቃት በኋላ ንግቶት በሌላ መንገድ ተመለሰ፡፡

                

የካህናት ሥልጣናቸው የማይናቅ፣ ትእዛዛቸውም ክብር የሚገባው መሆኑን ስለሚያውቅ ያመልአክ ወደ ላይም ወደታችም ሳይል አሥር ዓመት ከዚያው ሥፍራ ቆሞ ኖረ ፡፡ አሥር ዓመት ሲሆናት ለባል ታጨች ያጠመቅካት ብላቴና እነሆ ለአቅመ ሔዋን ፣ባል ልታገባ ነውና መጥተህ ባርከህ ስደዳት ብለው ለዮሐንስ አፈወርቅ ላኩበት፡፡ እርሱም በጥሪው መሠረት ከዛሬ አሥር ዓመት ልጅቱን ሊያጠምቅ ሲሔድ በሄደበት መንገድ መልአኩንቆሞ አገኘው፡፡ «ምነው ከዚህ ቆመሃል?» አለው ፡፡መልአኩም ሲመልስለት «የካህናት ማዕረጋቸው የከበረ ነውና መች ወዲያ ወዲህ ያሰኛል፡ ፡ቃልህን አክብሬ አንተ ቆይ ካልከኝ ወዲያና ወዲህ ብዬ አላውቅም»  አለው ቅዱስ ዮሐንስም በዝንጉዕነቱ ራሱን ወቅሶ መልአኩን የታዘዘውን ያደርግ ዘንድ አሰናብቶታል፡፡ ከላይ በተገለጸው ታሪክ ብናይ በፍጥሞ ደሴት መልአኩ ለዮሐንስ ወንጌላዊ አትስገድልኝ ማለቱ ዮሐንስ ካህንም ነውና ሥልጣኑ ሊያከብር እንደሚገባው ለመግለጽ ሽቶ ነው፡፡ በክብር ዮሐንስ ከመልአኩ ይበልጣልና፡፡

እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ‹‹አትስገድልኝ››ራእ.19፥10
bottom of page