top of page

ነገረ ድህነት

  • መቅድም 

  • ድኅነት ምን ማለት ነው

  • ሰው የዳነው እንደት ነው

  • ሰው ለመዳን ምን ያስፈልገዋል

  • የእያንዳንዱ ሰው ድህኅነት በራሱ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ

መቅድም 

የመዳን ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ማዕከል ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የሌሎች መጻሕፍት ዋና ዓላማ ሰው የሚድንበትን መንገድ ማሳየት ነው፡፡ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም የሞተው የሰወን ልጅ ለማዳን ነው፡፡

 

 «ነገር» የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የአንድን ትምህርት መስክ መግለጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ «ነገር ማርያም» ሲል ስለ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የገለጸውን ሁሉ የምንማርበት ትምህርት ማለት ነው፡፡ በዚህ ይዘቱ /LOGY/ የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ይመስላል፡፡ 

ድኅነት

በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ድኀነት ማለት ከኀጢአት ተፈውሶ የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሽ መሆንማለት ነው፡፡

«ሕዝቡንከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ» ማቴ. 1፤21፡፡ የነገረ ድኀነት ትምህርት ባንድ ወገንአባታችን አዳም ከወደቀበት የኀጢአት ማጥ ወጥቶ እንዴት ዳነ በሌላው ወገን ደግሞ እኛ ልጆቹስ እንዴት እንድናለን የሚሉትን ነጥቦች የምናይበት ትምህርት ነው፡፡ የነገረ ድኀነት መነሻው የአዳም ውድቀት ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ኃጢአትን የሠራ፤ ይድን ዘንድም ቃል ኪዳን የተገባለት የመጀመሪያው ሰው እርሱ ነውና፡፡ በመሆኑም ትምህርታችንን የምንጀምረው ከዚሁ ነው፡፡  የመናፍቃን የክህደት መነሻ ትክክለኛውን የመዳን መንገድ በመሳትና በማሳት በመሆኑ የቀድሞ ዘመን ጀምሮ አበው ምሥጢረ ሥጋዌን አምልተውና አስፍተው በማስተማርና በመጻፍ ነገረ ድኀነትን የትምህርታቸው መነሻና መድረሻ አድርገውታል፡፡

bottom of page