top of page

ለምን ቤተክርስቲያንን እንሳለማለን [እንሰግዳለን]

ለምን ቤተክርስቲያንን እንሳለማለን [እንሰግዳለን]
 

በሕንጻው ቤተ እግዚአብሔር ተገኝተን እንሳለማለን እንሰግዳለን ይኸውም ለባለቤቱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግልጽ ነው:: የመሳለማችን ወይም የመስገዳችን ምስጢር በቤተ እግዚአብሔር ፊት ስለሆነ የምንሰግደው ለአግዚአብሔር እንጂ ለሕንጻው አይደለም ወይም ለድንጋዩ አይደለም::

ዘጸ 33:10 "ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር። ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።"

2ኛዜና 7:1-3 "የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ። እርሱ መልካም ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።"

2ኛሳሙ 12:20 "ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ።"

መዝ 5:7 "እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።"

መዝ 29:2 "የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።"

መዝ 96:9 "በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ"

መዝ 132:7 "ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።"

መዝ 138:2 "ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።"

ሕዝ 46:1-2 "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ....አለቃውም በስተውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ"

1ኛነገ 9:3 "ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት...ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርም አለው፦ በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።"

ሐዋ 18:22 "ወደ ቂሣርያም በደረሰ ጊዜ ወጥቶ ለቤተክርስቲያን ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ።"

bottom of page