ደብረ መዊዕ ቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ እስጢፋኖስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
Ethiopian Orthodox church (EOTC) Phoenix, Arizona

የቤተ ክርስቲያናችን አመሠራረት
በመላው አሜሪካ እና በአሪዞና ግዛት ቀዳሚ እና ብቸኛ የሆነው ደብረ መዊዕ ቅዱስ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጉሜን ፬ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በወቅቱ የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ተመሠረተ። ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ደግሞ የካቲት ፲፩ ቀን ፪ሺ፬ ዓ.ም በብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ የወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ ተመረቀ። በቀድሞው የካሬቢያንና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ይስሐቅ መጥቶ ለበርካታ ዓመታት ስካትስዴል አሪዞና በሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአደራ ተቀምጦ የነበረው የቅድስት ሥላሴ ታቦት ግንቦት ፳፭ ቀን ፪ሺ፬ ዓ.ም. ወደ ቤተክርስቲያናችን ገባ። ሰኔ ፳፭ ቀን ፪ሺ፱ ዓ.ም. በብጹዕ አቡነ ፋኑኤል የዲሲ እና አካባቢው እንዲሁም የካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ የቤተክርስቲያናችን ስያሜ ደብረ መዊዕ ቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተብሎ እንዲስተካከል ተደረገ።
ትምህርት እና ስብከቶች
ሃሳብዎትን ያካፍሉን

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ
ደብረ መዊዕ ቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓላማ በፊኒክስ እና አካባቢዋ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን በሙሉ ማገልገልና በጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ይህችን እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት እና ሥርዓት ጠብቆ በማስተማር ለመጪው ትውልድ ማስረከብ ነው።

"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ።" (፪ቆሮ ፱፥፯)

